ለድሬዳዋ ነዋሪዋች ከአስተዳደሩ ከንቲባ ከድር ጆሀር በከፌስ ቡክ ገፃቸው ያስተላለፉት መልዕክት።

    በአስተዳደራችን የሚከበረው 16ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል፤ መላው የድሬዳዋ ነዋሪዎች፤ የአገራችንን በርካታ ውብ ዕሴቶች በአግባቡ እንድናውቅ፤ በወንድማማችነት መንፈስ ኢትዮጵያዊ ህብረታችንን ይበልጥ እንድናጎለብት፤ እንዲሁም… የእኛ የድሬዳዋውያን መገለጫ የሆነውን፤ በፍቅር እንግዳ የመቀበል መልካም ዕሴታችንን ይበልጥ እንድናጠናክር መልካም አጋጣሚ ይፈጥርልናል።
    በትውልዶች ታሪክ የማይረሳ አስነዋሪ ድርጊት የፈፀመው አሸባሪው የህወሓት አረመኔ ቡድን፤ በኢትዮጵያውያን ብርቱ ክንድ ግብዓተ መሬቱ እየተፈፀመ በሚገኝበትና፤ መላው ኢትዮጵያዊያን በችግር ጊዜ በአንድነት የምንቆም ጽኑ ህዝቦች መሆናችንን፤ ለአለም በተግባር ባሳየንበት በዚህ ወቅት መከበሩ በዓሉን ልዩ ያደርገዋል።
    የፀጥታ አካላት፤ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትና ግለሰቦች፤ እንዲሁም የንግዱ ማህበረሰብ፤ በአጠቃላይ መላው የድሬዳዋ ነዋሪዎች ለበዓሉ ስኬት የድርሻችሁን ጠጠር በመጣል ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ ጥሪ እያቀረብኩ፤ በአስተዳደራችን ከዚህ ቀደም በሌብነት ሂደት ተከናውነው ህጋዊ የመሠሉ፤ በርካታ ህገ-ወጥ ድርጊቶችና ብልሹ አሰራሮችን በማፅዳት፤ የጀመርነውን አስተዳደራዊ የልማትና የዴሞክራሲ ጉዞ፤ ከበዓሉ ማግስት ጀምሮ አጠናክረን እንደምንቀጥል አረጋግጥላችኋለው።
    #ወንድማማችነት ለሕብረ-ብሔራዊ #አንድነት