የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሰራተኞች እንደ ሀገር በተፈጠረው ወቅታዊ ሁኔታ ከቤታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የአልባሳት ድጋፍ በአስተዳደሩ ለተዋቀረው የሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ደረጀ ፀጋዬ አስረክበዋል።

    የሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ደረጀ ፀጋዬ በርክክብ ስነ ስርአቱ ላይ እንደተናገሩት መንግስት ያደረገውን ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎ ለወገን ደራሽ መሆናችሁን በራሳችሁ ተነሳሽነት በማድረጋችሁ በአስተዳደሩ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።