ጉዳዩን አስመልክቶ የድሬደዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን፣ ሊ ኢቭንት ኦርጋናይዘር እንዲሁም የድሬደዋ አትሌቲክስ ፌድሬሽን በጋራ መግለጫ ሰተዋል።
የፕሮግራሙ መዘጋጀት ለድሬደዋ መልካም ገፅታ ለመገንባት የሚኖረው ሚና ከፍተኛ ነው ያሉት የአስተዳደሩ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮምሽነር አቶ ፊራኦል ቡልቻ ናቸው።አንድነትን ከማጠናከር እንዲሁም ለሃገራችን በጋራ መቆም እንደሚገባን አመላካች ምሳሌ የሆነ ዝገጅት መሆኑን ኮሚሽነሩ ጨምረው ገልጸዋል::
አባይ ግድብ የህልውናችን መሰረት ነው ግድቡን እኛው ጀምረን እኛው መጨረስ እንደሚገባ ለዚህም ሁላችንም የበኩላችንን አስተዋፅኦ ማድረግ እንዳለብን ለማመላከት የተዘጋጀ የሩጫ ስነስርዓት መሆኑን ሊ ኢቭንት ኦርጋናይዘር ማናጀር ዳዊት አለሙ ተናገርዋል።


