በዛሬው ዕለት መነሻውንም መድረሻውም በምድር ባቡር አደባባይ ያደረገው “ደግሞ ለአባይ 7 ኪሎ ሜትር ሩጫ” የአስተዳደሩ ከንቲባ የተከበሩ ከድር ጆሀር አስጀምረዋል።
ከንቲባ ከድር በውድድሩ ላይ ባደረጉት ንግግር የስፖርት ቤተሰብ የግድቡን ግንባታ በማሳካት የቀጣዩን ትውልድ ህልውና የማረጋገጥና የማስቀጠል ኃላፊነቱን በመወጣት ታላቅ ሀገራዊ ፉይዳ ያለው ፖሮጀክት ለመጠናቀቁ ኃላፊነታችሁን ለመወጣት እያደረጉት ላለው አስተዋጽኦ በአስተዳደሩ ስም ምስጋና አቅርበ።
የአስተዳደሩ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮምሽነር ፊራኦል ቡልቻ በበኩላቸው ውድድሩ መካሄዱ ለድሬደዋ ያሏትን መልካም ገፅታ ለመገንባት የሚኖረው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል።
በውድድሩ የተሳተፉ ተሳታፊዋች በሰጡት አስተያየት በሀገራችን እየተገነባ ላለው ትልቁና ጉዙፍ ኘሮጀክት የድርሻችንን ኃላፊነት እንወጣለን ብለዋል።
በ3 ምድብ ተከፍሎ የተድረገውን የሩጫ ውድድር ከ1ኛ እስከ 3ኛ በመሆን አሸናፊ ለሆኑ የተዘጋጀላቸውን የሜዳሊያ ሽልማት የአስተዳደሩ የመንግስት ተጠሪ አቶ ደረጀ ፀጋዬ ሽልማቶች ተበርክቶላቸዋል ፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት አቶ ፉራኦል ቡልቻ ” ለውድድሩ መሳካት አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላትን አመስግነዋል ፡:”
የድሬደዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ፣ ሊ ኢቭንት ኦርጋናይዘር እንዲሁም የድሬደዋ አትሌቲክስ ፌድሬሽን በጋራ የተዘጋጀ የጉዳና የሩጫ ውድድር ሲሆን ቢጅ አይ ኢትዮጵያ ለዝግጅቱ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በድርጅቱ ለተደረገው ድጋፍም በአስተዳደሩ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ምስጋና ተችሮታል ፡፡፡


