በድሬዳዋ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ውይይት ተካሄደ። የድሬዳዋ አስተዳደር በትናንትና እለት ከከተማ ቀበሌዎች ከተውጣጡ የነዋሪዎች ተወካዮና ከአሰሪና ሰራተኞች ማህበራት ጋር በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር ተካሄዶል ።

    በመድረኩ ከወቅታዊው ሁኔታ አንፃር አካታች አገራዊ ምክክር የማድረግ አስፈላጊነት እና የከተማችን ነዋሪዎች እንዲሁም፤ የአሰሪና ሰራተኞች ማህበራት ሊኖራቸው በሚገባው ሚና ዙሪያ ውይይት በማድረግ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።
    በተመሳሳይም በዛሬው እለት በአስተዳደሩ ከሚገኙ የተለያዩ ወጣቶችና ሴት አደረጃጀት አባላት ጋር፤ በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር ተካሂዷል።
    በመድረኩ ከወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ አንፃር፤ የአስተዳደራችን ወጣቶችና ሴቶች ሊኖራቸው የሚገባው ሚና ምን ሊሆን እንደሚገባ በመወያየት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።