ዛሬ በተፈጠረው 5 የተለያዩ የህዝብ አደረጃጀት መድረኮች ላይ የአስተዳደሩ ም/ከንቲባና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የመምህራንና የር/መምህራን፣ የንግዱ ማህበረሰብ፣ የወጣቶችና ሴቶች አደረጃጀቶች፣ የሀይማነት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች እና የአካል ጉዳተኞችና ሲቪክ ማህበራት መድረኮች ተካሂደዋል።
በተካሄደው መድረኮች ህዝቡ በህልውና ትግሉ የተገኙ ድሎችና በድህረ ጦርነት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች ላይ ኢትዮጵያውያን በተባበረ ክንድ ጠላትን አሸንፈው በጦርነቱ የተወረሩ አካባቢዎችን ሙሉበሙሉ ነፃ በማውጣት ዘላቂ ሰላምና ነጻነት እንዲኖር ሁሉም ባለበት የህዝብ አደረጃጀት ኃላፊነት መወጣት እንደሚገባ ተገልጿል።
ተሳታፊዎች በማከልም የተገኘው ድል የህዝቡ መሆኑን በመግለጽ ከጦርነቱ በኋላ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የውስጥና የውጭ ችግሮችን ለመከላከልና ለመመከት ከወዲሁ ተደጋጋሚ ውይይት ማድረግና መፍትሄ ማስቀመጥ ተገቢ ነውም ብለዋል፡፡


