የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ ከድር ጆሀር ለክርስትና እምነት ተከታዮች ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

    በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ከሚከበሩ ታላላቅ በዓላት አንዱና ዋነኛው የገና በዓል ነ ው! የዘንድሮ የገና በዓል አገራችን ኢትዮጵያ ምንም እንኳን የእናት ጡት ነካሾች ቢፈታተኗትም ድልን እየተቀዳጀችበት ባለበት ወቅት መከበሩ በዓሉን ለየት የሚያደርገው ነው፡፡
    ይህ ብቻ አይደለም፡፡ ክቡር ጠሚኒስትራችን ዶ/ር አብይ አህመድ ለዲያስፖራው ባቀረቡት ጥሪ መሠረት በርካታ ዲያስፖራዎች ከአገሬ የሚበልጥ የለም ብለው በአገራቸው የተገኙበት ጊዜ መሆኑ የዘንድሮውን የገና በዓል የተለየ ውበት የሚሰጠው ነው፡፡
    ውድ የአስተዳደራችን ነዋሪዎችና የክርስትና እምነት ተከታዮች በዓሉን ስናከብር እንደ ወትሮው ሁሉ የተቸገሩት በመርዳትና ካለን ላይ ብቻ ሳይሆን ከሌለንም ላይ ቢሆን ወገኖቻችንን በማሰብ በፀና አለት ላይ የተመሰረተው ኢትዮጵያዊነታችንን እንድናሳይ መልዕክቴ ይድረሳችሁ እላለሁ!
    መልካም የገና በዓል!