በዓሉ በተለይም ዘንድሮ በብዙ ድሎቻችን ታጅቦ፤ በኢትዮጵያዊነትና በህብረብሔራዊ አንድነት አምሮና ተንቆጥቁጦ የሚከበር በአል ነው ሲሉም ገልፀውታል፡፡
ለእናት ሃገራችን ኢትዮጵያ ክፉዋን የሚመኙትን አሳፍሮ ለህመምዋ ሳይሆን ለፈውሷ የሚተጉን ልጆቿ ክንድ አበርትታ የተከፈተባትን ወረራና ጦርነት በመመከትና ይበተናሉ ፣ ይፈርሳሉ ሲሉን በአንድነትና በፅናት በመቆም ወራሪዎችን እንድናሳፍር የረዳን ፈጣሪ ምስጋና አቅርበዋል።
በዓሉ ስናከብር በንፁሃን ላይ ባደረሰባቸው ሰቆቃና መከራ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ያሉ ወገኖቻችንን የምንደግፍበት የምናበረታታበት እና ከጎናቸው መሆናቸውን የምንገልፅበት የምናስብበት እንዲሆን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ልጆቾን ይጠብቅ
መልካም የገና በዓል


