<<ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ2014 ዓ.ም የገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት በዓሉ የሰላም፣የደስታ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ!>>

    የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ
    ይህን ታላቅ በዓል ስናከብር የጁንታውን ቡድን ለመጨረሻ ጊዜ ከእኛ ከኢትዮጵውያን ጫንቃ ላይ ለማላቀቅ ያሳየነውን አንድነትና መተሳሰብ በኢኮኖሚውም ዘርፍ በማሳየት መሆን ይኖርበታል፡፡ የጁንታውና የከሀዲው የህወሓት ቡድን አንዱ ስትራቴጂ በገበያው ላይ ሰውሰራሽ የዋጋ ንረት በመፍጠር መንግስትና ህዝብ ላይ ጫና ለመፍጠር በመሆኑ በዚህ ታላቅ በዓልም ሆነ ከበዓሉ ውጪ ባሉት ጊዜያት ከአግባብ ውጪ የሆነ የዋጋ ጭማሪ ባለማድረግ ሀገራዊ ሃላፊነታችንን እንድወጣ መልዕክቴ ነው፡፡
    መልካም የገና በዓል