የአስተዳደሩ መምህራን በድህረ ጦርነት ስትራቴጂ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ ገለጹ።

    በአስተዳደሩ የሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤት መምህራን በድህረ ጦርነት ወቅት ሊያጋጥሙ ሁኔታዎችን እና ክስተቶችን በአግባቡ በመረዳት ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል።
    መምህራኖቹ በጦርነት የተገኙ ድሎች ሳያኩራሩን ለቀጣይ ወይም ከፊታችን ለሚያጋጥመን ፈተና ዝግጁ መሆን አለብንም ብለዋል፡፡
    አክለውም በህብረ ብሄራዊ አንድነት ዘመቻ ኢትዮጵያውያን በጥምረት ቅንጅታዊ አሰራርን በመከተል ባገኙት ድሎች፣ በአጋጠሙ ጉድለቶች እና በቀጣይ በመማር ማስተማር ምን መሰራት ይኖርበታል በሚሉ ሃሳቦች ዙሪያ ምክክር የተደረገ ሲሆን ድል ጠብቆ በሌሎች የልማት መስኮች የህዝብ አንድነትና ጥንካሬን ማስቀጠል እንደሚገባ ተነስቷል፡፡
    በዛሬው ዕለት በነበረው መድረክ የፓርቲው ም/ኃላፊና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሻኪር አህመድ እና የልማታዊ ቷማት ክትትልና ድጋፍ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኡመር አህመድ በተገኙበት ሰፊ ሃሳቦች በማንሳት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
    ምንጭ፦Dire_PP_Press