የአረመኔውን ህወኀት ሰይጣናዊ ተግባር በአካል ተመለከትን። ጁንታው ድልድዩን ቢሰብረውም፤ በጀግናው የህዝብ ሰራዊት ድልድይነት የጭቃውን ፈተና አልፈን የደጀንነት ስጦታችንን ሀራ ላይ አስረከበናል። የምድር ድሮኖቹ ጀግኖች፤ የ303ኛው ኮር የምስራቅ ዕዝ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በሚገኙበት ቡርቃ በአካል መገኘት ደስታው ልዩ ነው። የገናን በዓል ዋዜማ አብሮ ማሳለፍ መቻል ደግሞ እጥፍ ድርብ ደስታን ይሰጣል። ትናንትም ዛሬም ወደፊትም የድሬዳዋ አስተዳደር የጀግናው ሰራዊት ደጀን ሆኖ ይቀጥላል። የትኛውም ምድራዊ ሀይል ኢትዮጵያንና ልጆቿን ከብልፅግና ጉዞዋችን አይገታንም። ከአስተዳደሩ ከንቲባ ከድር ጆሀር ከማህበራዊ ትስስር ገፃቸው የተወሰደ።


