የአገር ጥሪን ተከትሎ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች እንደ ሃገር ከሚመጡ አንድ ሚሊየን ውስጥ ከ1000 በላይ የሚሆኑት ድሬዳዋ አስተዳደር ይመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል በዚህ መሰረት እስካሁን ከመቶ በላይ መግባታቸውን የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንሸስትመንት ቢሮ ሃላፊ አቶ ሃርቢ ቡህ ገልጸዋል ፡፡
ምክትል ከንቲባው ወደ ድሬደዋ የሚገቡትን ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎች ሙሉ እንቅስቃሴ ለማስተባበር በምክትል ከንቲባው የሚመራ አብይ ኮሚቴ ተዋቅሮ አየተሰራ መሆኑን አቶ ሃርቢ ጨምረው ገልፀዋል።
በቀጣይ የሚከናወኑ ሁነቶችን በዝርዝር አብራርተዋል በዚህ መሰረት :-
– ዲያስፖራዎች ወደ ድሬዳዋ ሲገቡ በድሬዳዋ እሴት ለመቀበልና ለማስተናገድ በቂ ዝግጅት ተደርጓል፡፡
– እንግዶች የሚያርፉባቸው ሆቴሎች 25-30% እንዲቀንሱ መግባባት ላይ መደረሱንና በዛው ልክ እያስተናገዱ መሆኑን።
– ዲያስፖራዎች በማህበራዊ ድጋፍ እንዲሰማሩ ይደረጋሉ፡፡
– በቀጣይ የልማት ሲንፖዚየም የድሬዳዋን የአሁናዊ ሁኔታና የቀጣይ ተስፋዎችን የሚያሳይ እንዲሁም ከዚህ ቀደም በዲያስፖራ የተሰሩ ልማቶችን ያካተተ ሰነድ የሚቀርብበት ሲንፖዚየም ይኖራል፡፡
– የምስጋናና የእራት ግብዣ
– ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎች የሚሳተፉበት ታላቁ ሩጫ ይካሄዳል።
– በቀጣይ ዲያስፖራው የሚያደርገውን ድጋፍ የተቀናጀና ወጥነት ባለው መልኩ ለማካሄድ ስራ በጥንካሬ ይሰራል


