ከወጣቶቹ ጋር በመወያየት፤ ስራቸውን በህጋዊ መንገድ መቀጠል እንዲችሉ ከመግባባት ደርሰን፤ የስራ መመሪያ ተሰጥቷል። ልዩነቶቻችንን በውይይት በመፍታት፤ የተበላሹ እና ህገወጥ ተግባራትን ስርዓት እያስያዝን፤ ወጣቶችን የድሬዳዋ የለውጥና የእድገት ኃይሎች ማድረጋችንን እንቀጥላለን።
ሰሞኑን በ03 ቀበሌ ገንደ ዲፖ/ገንደ ሮቃ አካባቢ በተከናወነ ህግ የማስከበር ተግባር ምክንያት፤ በአካባቢው ተደራጅተው በሚሰሩ ወጣቶች ላይ ቅሬታ መፈጠሩን ተረድቻለሁ።


