በድሬደዋ ገንደ ገበሬ እና ሌሎች ገጠር ቀበሌዎች ሽብር በመፍጠር እንዲሁም በፀጥታ አካላት ላይ ጥቃትቃት ያደረሱ 5 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎችን ጨምሮ በተለያዩ መንገዶች ለሽብር ቡድኑ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ 24 ተጠርጠሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የምስራቅ ኢትዮጵያ የፀትታ ኮማንድ ፖስት ዛራ አስታውቋል።
ኮማንድ ፖስቱ ለጋዜጠኞች በሰጠው የጋራ መግለጫ የድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ኮምሽነር አቶ አለሙ መግራ የሽብር ቡድኑ አባላት ታህሳስ 14 /2014 በቢዮ አዋሌ ክላስተር በፀጥታ አካላት ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን አስታውሰው በፀትታ አካለት በተጠናከረ ቅንጅት በተደረገ ዘመቻ የሽብር ቡድኑ ተጨማሪ ገዳት ሳያደርስ መበታተኑን ተናግረዋል።
በመቀጠልም አባላቱ እራሳቸውን በመቀየር እና ሰላማዊ ሰው በመምሰል ወደ ህዝቡ ለመቀላቀል መሞከራቸውን፣በተለይም የሽብር ቡድኑ መሪ ፉአድ ሃሰን ኢብራሂም /ጃል ኦዳ/ እራሱን ቀይሮ ወደ ሃረር ከተማ መሸሹን ኮምሽነር አለሙ አብራርተዋል።
ይሁን እንጂ የመከላከያ ሰራዊት፣ፌደራል ፖሊስ፣ብሄራዊ የመረጃና ደህንነት ኤጀንሲ፣አየር ሃይል፣የድሬደዋ ፍትህ ፀትታና ህግጉዳዮች ቢሮ አንዲሁም የድሬደዋ ፖሊስ ኮሚሽን በጋራ በመሆን ባካሄዱት ዘመቻ የሽብር ቡድኑ መሪ ፉአድ ሃሰን ኢብራሂም በቅጥል ስሙ ጃል ኦዳ ተብሎ የሚጠራው ግለሰብ ሃረር ላይ በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ በደረገው ምርመራ ሌሎች 4 የሽብር ቡድኑ አባላትን እንዲሁም በተለያዩ መንገዶች ለሽብር ቡድኑ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ 24 ተጠርጠሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኮሚሽነር አለሙ አብራርተዋል።
አሁን ላይ በድሬደዋ ጥቃትና ሽብር ለማድረስ የሚችል የታጠቀ የኦነግ ሸኔ ቡድን አለመኖሩን ኮሚሽን አለሙ በመግለጫቸው አረጋግጠዋል።
በሌላ በኩል በፌደራል ፖሊስ ምስራቅ ቀጠና ወንጀል ምርመራ ዲቪዥን ሃላፊ ምክትል ኢኒስፔክተር ለሜሳ መኮንን ከኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን ጋር ተያይዞ በተደረገ የወንጀል ምርመራ የፌደራል ፖሊስ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት ኤጀንሲ፣ከድሬደዋ ፖሊስ ኮሚሽን ገር በጋራ በመሆን 24 ተጠርጠሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ መጀመሩ ገልፀዋል።
ከሽብር ቡድኑ መሪ ጃል ኦዳ /ፉአድ ሃሰን ኢብራሂም/ ጋር በእግዚቢትንት የተያዙ መሳሪያዎችን እና ቁሳቁሶችን በዝርዝር ያብራሩ ሲሆን በዚ መሰረት:-
* የጦር መሳሪያዎች / ክላሾች
* በርካታ ቁጥር ያላቸው የክላሽና የብሬል ጥይቶች
*የክላሽ ካዝናዎች
*የእጅ ቦንቦች
*ጂም ሲሪ መሳሪያዎች እና ጥይቶች
*የወታደር መገናኛ ሬዲዮ
*የጦር መሳሪያ መነፅር
*የወታደር ትጥቆች እንዲሁም ለመጀመሪያ እርዳታ የሚውሉ ቁሳቁሶች፣የምግብ ቀለቦች፣ስለቶች እና ብዛት ጃላቸው የውሃ ኮዳዎች ጥር 3 /2014 ዓም በኤግዚቢትነት መያዛቸውን ምክትል ኢንስፔክተሩ አብራርተዋል።
የሽብር ቡድኑ አባላትን በቁጥጥር ስር በማዋሉ ሂደት ህብረተሰቡ ከፍተኛ ድጋፍ ሲያደርግ እንደነበር የገለጹት ምክትል ኢንስፔክተር ለሜሳ በቀጣይም ሰላምን በማወክ የሽብር ተግባር ለማከናወን የሚጥሩ ቡድኖችን ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን መከላከል ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅረበዋል።ተጨማሪ የምር መራ ውጤቶችን ለህዝብ ይፋ እንደሚደረጉ ምክትል ኢንስፔክተር ለሜሳ መኮንን ጠቁመዋል።


