የአስተዳደሩ ከንቲባ ከድር ጆሀር በምስጋና ፖሮግራሙ እንደተናገሩት ጥቂት ብንዘገይም፤ እጅግ ለምንወዳቸው የቀድሞ ከንቲባችንና ወንድማችን አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ ዛሬ ያደረግነው ሽኝትና የሰጠነው ስጦታ፤ በአመራርነት ዘመኑ ካደረጉት አሰተወፅኦ አንፃር ለሳቸው ያንስባቸዋል እንጂ አይበዛም ብለዋል።
በአመራርነት ዘመናቸው ላደረጉት አስተዋፅኦና መልካም ስራዋች ሁሉ የአስተዳደሩ ከንቲባ ከድር በራሴና በድሬዳዋ ህዝብ ስም አክብሮትና ምስጋናዬን አቀርባለሁ ሲሉ አመስግነዋል ።
ለኘሮግራሙ መሳካት ከአስተዳደሩ ጎን ለነበሩ ሁሉ ከንቲባ ከድር አመስግነዋል።


