ከበአሉ አከባበር ጋር ተያይዞ የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀርና ኮሚሽነር አለሙ መግራ ከኢ/ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት አባቶች ጋር የጋራ የውይይት መድረክ አካሂደዋል ።
በሀይማኖት አባቶች ፀሎትና ምርቃ በጀመረው የጋራ የውይይት መድረክ የተገኙት የድ/ዳ/አስ/ ከንቲባ አቶ ከድር ጀዋር በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የጥምቀት በአል በድ/ዳ የሀይማኖቱ ተከታዮች ብቻ ሳይሆኑ የሌሎችም እምነት ተከታይ የሆኑ ወንድሞች ለረጅም ግዜያት በገነቡት ድሬደዋዊ የአብሮነት እሴት ለበአሉ የድርሻቸውን የሚያበረክቱበትና አብረው የሚያከብሩት በአል ነው ሲሉ ነው ከንቲባው የተናገሩት :
በእዚህም የዘንድሮው የጥምቀት በአል ሠላማዊ በሆነ መልኩ እንዲከበር አስተዳደሩ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ተናግረው ህዝበ ምእመኑም ሆነ መላው የአስተዳደሩ ነዋሪ ዛሬም ሰላማችን እንዲደፈርስና የእርስ በእርስ ግጭት እንዲነሳ ከሚሹ ሀይሎች እኩይ ሴራና ከፋፋይ የግጭት ሀሳቦች እራሱን በመጠበቅና በማራቅ ብሎም እኩይ ተግባራቸውን በማክሸፍ ለበአሉ ሰላማዊነት የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ነው ያሉት::
በውይይቱ የተገኙት የቅድስት ቤተክርስቲያኗ የቤተ ክህነት፣የየአድባራቱ አስተዳዳሪዎችና፣የእምነት አባቶች በበኩላቸው አስተዳደሩም ሆነ የድሬዳዋ ፖሊስ ባለፉት ሁለት አመታት ለበአሉ ሰላማዊነትና ላከተማዋ ሠላም መረጋገጥ እያከናወነ ላለው ስራ ምስጋና አቅርበው የዘንድሮው በአል በሀይማኖታዊ ስርአቱ መሰረት የለምንም ችግር እንዲከበር ለምእመኑ የተለያዩ ሀይማኖታዊ አስተምህሮትን ከመስጠት ጀምሮ ለበዓሉ ደምቀትና ሠላማዊነት የበኩላቸውን እያተወጡ መሆኑን ነው የተናገሩት ።
የሀይማኖት አባቶቹ ህዝበ ምዕመኑ ከቤተክርስቲያኗና ከሀይማኖት አባቶቹ የሚተላለፉ መልዕክቶችን በመቀበልና በመተግበር እንደ ከእዚሂ ቀደሙ ሁሉ በመጪው ጥምቀትም ሃላፊነቱን ሊወጣ ይገባልም ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል::
የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽነር አለሙ መግራ በበኩላቸው የድሬደዋ ህዝብ የፍቅርና የሰላም መገለጫ የሆነና ሁሉንም በአላት አንዱ ከሌላው ጋር በቤተሰባዊነት የሚያከብረው እንደሆነ ተናግረው መጪው የጥምቀት በአል ምንም አይነት የፀጥታ መደፍረስም ይሆን ሁከትና ረብሻ ሳይፈጥር ፍፁም ሠላማዊ ሆኖ ተከብሮ እንዲያልፍ በመላው የፀጥታ አካላት ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ገልፀዋል::
ኮሚሽነሩ አክለውም የበአሉን ሰላምና ፀጥታን በአስተማማኝ ደረጃ ከማረጋገጥ ጎን ለጎን በዓሉ በተለይ መልኩ በድምቀት እንዲከበር ለማስቻል የድ/ዳ ፖሊስ ልዮ የፈረስ እጀባን በበአሉ እንደሚያከናውንም ተናግረዋል ።
በውይይት መድረክ ማጠናቀቂ ላይም በተደረሰ የጋራ መግባባት ከበአሉ ጋር ተያይዞ መግባቢያ ላይ የተደረሰባቸውና ሀሳብና ነጥቦች የተገለፁ ሲሆን በእዚሁ መሰረት
1ኛ- ከበአሉ ጋር ተያይዞ ከቅ/ቤተክርስቲያኗ እና ከሀገሪቱ የፌደራል ሰንደ ቃላማ ውጪ ምንም አይነት ሰንደ-ቃላማን መጠቀምም ሆነ ይዞ መንቀሳቀስ እንደ ማይቻል:;
2- በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች፣መንገዶች፣ አደባባዮችና መሰል ስፍራና ቦታዎች ላይ ምንም አይነት ቀለም መቀባት የተከለከለ መሆኑ ተገልፆል::
የድሬደዋ ፖሊስ ከበአሉ ጋር ተያይዞ ዝርዝር የጥንቃቄ መልዕክትችና ክልከላዎችን በተመለከተ ለመላው ህ/ብና የሚዲያ አካላት ከበአሉ ቀደም ብሎ የሚያሳውቅም ይሆናል::


