የድሬደዋ ፖሊስ እንዳስታወቀው በሀይማኖታዊ ስርአቱ መሰረት ሁሉም ታቦታት በዝምሬና ምስጋና በሰላም ወደ የደብራቸው በሰላም መግባታቸውን ገልፆ ለበዓሉ ፍፁም ሰላማዊነት ምስጋናውን አቅርቧል::
ከጥምቀትና ከተራ በአል አከባበር ጋር ተያይዞ ለበአሉ ፍፁም ሰላማዊነት አስቀድሞ የበአል የፀጥታ እቅድ በማውጣት ወደ ስራ መግባቱን የገለፀው ፖሊስ በጥምቀት ሆነ ከተራ በአል ምንም አይነት የፀጥታ ችግርም ሆነ የወንጀል ተግባራት ሳይፈፀሙ እንዲሁም የትራፊክ አደጋ ሳይከሰት ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ መከበሩን ነው ያስታወቀው::
ፖሊስ ጨምሮ እንዳስታወቀው በድሬደዋ ካለፉት ሶስት አመታት ወዲሂ በአስተዳደሩ በሚከበሩ ሀይማኖታዊም ሆነ ህዝባዊ በአላት ብሎም በእለት ተእለት የህ/ብ እንቅስቃሴ ምንም አይነት የፀጥታ ችግር እንዳይከሰትና እንዳያጋጥም መላው ህ/ብን ባሳተፈ መልኩ ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ ሀይሎችና ከአስተዳደሩ ጋር በሰራቸው ጠንካራ የህግ ማስከበርና ሰላምና ፀጥታን የማረጋገጥ ስራዎች ከፍተኛ ውጤቶችን ማምጣት አስችሏል ነው ያለው ፖሊስ በመግለጫው::
የዛሬውም የጥምቀት በዓል ፍፁም ሰላማዊነት የህዝባችንን ሰላም ወዳድነት፣አንድነትና ወንድማማችነት እንዲሆም አንዱ ከሌላው ጋር ያለውን በጋራ ተዋዶ የመኖር ባህልና እሴቱን ይበልጥ ያሳየና ያረጋገጠ ነው ሲሊም ፖሊስ ገልፃል:
ፖሊስ በመግለጫው በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበረውና በአለም አቀፉ የትምህርት የባህልና የሳይንስ ተቋም ዮኔስኮ በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገው ጥምቀት በዓል ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር ህዝበ ምእመኑ፣መላው የአስተዳደሩ ነዋሪ፣የፀጥታ ሀይሎችና ተቋማት፣አጋዥ የህ/ብ ክፍሎች እና የሰራዊቱ አባላት ለነበረቻው ትልቅ ድርሻና ተሳትፎ የድሬደዋ ፖሊስ ምስጋና አቅርቧል።


