የአስተዳደሩ ገቢዎች ባለስልጣን የግማሽ ዓመት የገቢ አፈፃፀም ከባለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር 55.18%ብልጫ መሳየቱ ተገለፀ፡፡

    የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም መሀመድ በ2014 በጀት ዓመት በግማሽ ዓመት የእቅድ አፈፃፀም አስመልክቶ ለጋዜጠኞች በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰተዋል።
    የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም መሀመድ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለ2014 በጀት ዓመት ከመንግስት ታክስ ብር 1,866,000,000.03 ከማዘጋጃ ቤት ብር 434,000,000.00 በጠቅላላው ብር 2,300,000,000.00 በበጀት ዓመቱ ለመሰብሰብ ማቀዱን ገልፀዋ፡፡
    የባለስልጣን መስሪያ ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም በግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ከመንግስት ታክስና ከማዘጋጃቤት ገቢ ብር 1,052,702,951.65 ለመሰብሰብ ታቅዶ 1,052,800,430.74 መሰብሰብ ተችሏል ብለዋል ፡፡
    የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም የግማሽ አመት አፈፃፀም ከታቀደው እቅድ አንፃር ሲታይ 100.01% መሆኑ በመጥቀስ
    የስድስት ወር የገቢ ዕቅድ አፈፃፀም ከዕቅድ አንፃር ሲታይ 0.01% ወይም በብር 97,479.09 ብልጫ አለው ብለዋል፡፡
    የ2014 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የገቢ አፈፃፀም ከባለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር 55.18% ወይም በብር 374,379,068.42 ብልጫ ማሳየቱን የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም ገልፀዋል።
    የባለስልጣን መስሪያ ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም
    ይህ አፈፃፀም ከጠቅላላው በጀት ዓመቱ ዕቅድ አንፃር ሲታ 45.77% ድርሻ እንዳለው አስታውቀዋል፡፡
    ለዕቅዱ መሳካት የአስተዳደሩ ታማኝ ግብር ከፋዬች ፣ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም የአስተዳደሩ ባለድርሻ አካላት ጋር በነበረው ቅንጅታዊ አሰራር ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት የተመዘገበ ውጤት መሆኑ የባለስልጣን መስሪያ ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም ገልፀዋል፡፡
    የአስተዳደሩ ከንቲባ የተከበሩ ከድር ጆሀርና የካብኔ አባላት የገቢ አሰባሰቡ ውጤታማ እንዲሆን ላደረጉት አስተዋፅኦ አቶ አብዱሰላም አመስግነዋል።