የድሬዳዋ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ
አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ
የአመራር የብቃት አቅምን ለማሳደግ ከጥር 16-18/2014 በድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ፖርቲ፣የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ እና የወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን በጋራ በመሆን ያዘጋጁት ስልጠና መሰጠት ተጀምሯል።
ለሦስት ተከታታይ ቀን በሚቆየው ስልጠና ላይ የድሬዳዋ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ እንደተናገሩት አጠቃላይ አመራሩ ከለውጡ ማግስት የተለያዩ ስራዋችን እየሰራ ቢቆይም ከተማችን ከ6ኛ ሀገራዊ ምርጫ ካካሄደች በኋላ ህዝቡ ያነሳቸው በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ ዘርፍ በርካታ ጥያቄዋች ያሉባት ከተማ በመሆኖ የምንመራው አመራሮች ችግሮችን በአግባቡ ተረድተን ለህዝብ የገባውን ቃል ወቅቱ የሚጠይቀወን የአመራርነት ክህሎትን በመላበስ እንዲችል የተዘጋጀ ነው ብለዋል።
የፖርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም አክለውም አመራሩ ከዚህ ስልጠና በኋላ ያገኘውን እውቀት ህዝብና መንግስት የጣሉበትን አደራ ተግባቡቶ ሀገር ሊለውጥ የጋራ እራይ የሰነቀ ሆኖ እንዲሰራ ይህ ስልጠና ትልቅ ፋይዳ አለው ብለዋል።
በአቅም ግንባታው ስልጠና ላይ የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ባደረጉት ንግግር ስልጠናው የአመራሩን አቅም በመገንባት ለስራቸው ውጤታማነት ትልቅ አስተዋጽኦ መኖሩን ጠቁመው አመራሮች የመሪነት ሚናቸውን እንዲያጎለብቱና በየጊዜው ከሚመጡ አዳዲስ የአመራር እሳቤዎች ጋር እራሳቸውን እንዲያስተዋውቁ እድል ይሰጣል ብለዋል፡፡
የአስተዳደሩ ከንቲባ ከድር ከዚህም ጋር አያይዘው የብልጽግና ፓርቲ አላማዎቹን ከግብ ማድረስ እንዲያስችለው የአመራሮች የመፈፀምና የማስፈፀም አቅማቸው እንዲዳብር ብሎም ፓርቲው ካስቀመጠው አቅጣጫ አንጻር አመራሮች እውቀታቸውንና ክህሎታቸውን እያሳደጉና እያሻሻሉ የልማት ጉዞአችንን ለማሳካት ብቃት ያላቸው ሆነው እንዲመሩ ለማስቻል የድሬዳዋ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ይህን ስልጠና አዘጋጅቷል ብለዋል፡፡
ከንቲባ ከድር ስልጠናው በፓርቲው ጽ/ቤት በተደረገ የዳሰሳ ጥናት መሠረት በተለዩ የስልጠና መስኮች በዘርፉ የካበተ ልምድና ከፍተኛ ብቃት ያላቸውን አሰልጣኞች በመጋበዝ ክፍተት በታየባቸው የመሪነት ዘርፎች ማለትም H ፋውንዴሽን ፣ኦፍ ሊደርሺፕ እና ዴቨሎፒንግ ሊደርሺፕ አቲትዩድ ርዕሶች ዙሪያ ስልጠናው መዘጋጀቱን ጠቁመዋል፡፡


