የኮንስትራክሽን ቤቶችና መዘጋጃቤታዊ ቋሚ ኮሚቴ የመንገዶች ባለስልጣንን የግማሽ ዓመት ሥራ አፈጻጸም፣ የስልሳ ቀን እቅድ አፈጻጸም እና በከተማም በገጠርም ከፕሮጀክቶች አፈጻጸም ዙሪያ የመስክ ምልከታ አካሂዷል፡፡
ቋሚ ኮሚቴው በባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ የስልሳ ቀን ዕቅድ አፈፃፀም እንዲሁም ከብሔር ብሔረሰቦች ጋር ተያይዞም የተሰሩ የከተማ የአስፋልት ጥገና 500 ሜትር ታቅዶ ከሁለት ኪሎ መጠገኑን፣ በከተማው የተለያዩ ጭለማ የነበሩ ቦታዎች ማብራት መቻሉን ቋሚ ኮሚቴው ገምግሟል፡፡ በተያያዘም በከተማ ሰፈር ውስጥ ለውስጥ የኮብል እስቶን ጥገና የዲሽ (የውሃ መውረጃ ቦይ) ጥገና መካሄዳቸውን ገምግሟል፡፡ ከታቀዱት አዲስ እና ነባር ፕሮጀክቶች በአጠቃላይ 22 ፕሮጀክቶች የአሸዋን መንገድ ጥገና የሀፍካት ቁጥር 2 ድልድይ ግንባታ 320 ኪሜ የኮሪሶ መንገድ ግንባታ እንዲሁም በሂደት ላይ ያለ የከተማ ውስጥ የትራፊክ መብራት ዝርጋታ ቋሚ ኮሚቴው በመስክ ምልከታው ገምግሟል፡፡
በተያያዘም 4.2 ኪሜ በ521 ሚሊየን ብር የሚሰራ ከ ሻም ሆቴል እስከ ዋናው የጅቡቲ መንገድ የመንገድ ዝርጋታ ይህም 10.24 በመቶ መጠናቀቁን እንዲሁም 470 ሜትር የከተማ ውስጥ የአስፋልት ግንባታ ቋሚ ኮሚቴው ተዘዋውሮ ተመልክቷል፡፡ ቋሚ ኮሚቴው ይህን ከገመገመ በኋላ የተሠሩት ሥራዎች ካለው የበጀት ውስንነትና ሌሎች ችግሮች አንጻር ጥሩና የሚያበረታ መሆኑን በመጠቆም የተበላሹ ማሽነሪዎችን ከማስጠገን፣ የሚሠሩ የመንገድ የስራ ጥራት ላይ እንዲሁም የከተማዋ ትራፊክ መጨናነቅ እና ያለውን የበጀት እጥረት መፍትሄ እንዲያበጁለት አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡


