ለቤቲንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ድሬዳዋ የመጡ የእግር ኳስ ቤተሰቦች በሙሉ ፍቅር ወደሆነችው ከተማችን ድሬዳዋ እንኳን በሰላም መጣችሁ ብለዋል ፡፡
የድሬዳዋ አስተዳርን በመወከል ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ እስቅያስ ታፈሰ የለውጡ አመራር በሁሉም ዘርፍ ድሬዳዋን ወደ ቀድሞ ከፍታዋ ለመመለስ በተያዘው አቅጣጫ በልዩ ትኩረት የውድድሩን በመመራቱ ዝግጀቱ መጠናቀቁን አሳውቀዋል ፡፡
ቤተኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በድሬዳዋ መከናወኑ ዘርፈብዙ የሆኑ (ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊና የድሬዳዋን መልካም ገጽታ )ከመገንባት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለው የገለጹት ኃላፊው የስፖርት ቤተሰቡ በድሬዳዋ በሚኖረው ቆይታ የድሬዳዋን የአብሮነት ፣ መደጋገፍና የፍቅር መናሀርያ መሆኗን ትዝታ ፈጥሮበት በሰላም እንዲመለስ የተለያዩ ሁነቶች በመሀል በመሀል ተዘጋጅተዋል ብለዋል ፡፡
ጸጥታን በሚመለከት ድሬዳዋ በቀርቡ ባሳለፍነው በዓል ዓለምን ማስደመም የቻለችበትን አጋጣሚ ተሞክሮ በማጠናከር ለስድስት ሳምንት የሚቆየው ውድድር ያለ ኮሽታ አእንዲጠናቀቅ ሁሉም የጸጥታ አካሎቻችን ዝግጅትተጠናቋል ሲሉ አቶ ህዝቅያስ የጸጥታ አካሉን ዝግጅት አረጋግጠዋል ፡፡
በመጨረሻም የበትኪንግ አመራሮችና ባለሙያዎች ፣ የየቡድኑ አመራሮችና ተጫዋቾች፣የሚዲያ አካላትና እንግዶች በድሬዳዋ የሚኖራቸው ቆይታ ያማረና የስኬት እንዲሆን ተመኝተዋል ፡፡
የወጣቶችን ስፖር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፍራውል ቡልቻ በስፖረቱ ዘርፍ የተደረጉ ዝግግቶችን የዘረዘሩ ሲሆን በአብይና በንዑሳን ኮሚቴዎች በማዋቀር የባለፈውን ዓመት ተሞክሮና ክፍተቶችን በሞላ መልኩ ዝግጅት መደረጉን አሳቀዋል ፡፡፡
ጤናን በሚመለከት በማዕከል እንዲመራ የተደረገ ሲሆን በመተንፈሻና በአጥንት ስፔሻላይዝድ ባደረጉ ባለሙያዎች እንዲደራጅ መደረጉን ፤ የጸጥታ አካሉ እንከን የማይወጣለትና ሊመሰገን የሚገባው መሆኑን ፤ማዘውተርያ ቦታን በሚመለከት ስታዲየሙ ምርጥ በሚባል ደረጃ መታደሱን ፣የመለማመጃ ሜዳዎች በበቂ ሁኔታ መዘጋጀታቸውን ፤ ከመስተንግዶ ጋር በተያያዘ ከባህልና ቱሪዝም ጋር በመሆን በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን አስታውቀው ይህን ሁሉ ዝግጅት ልናደርግ የቻልነው ለስፖርት ፍቅር ያለው አስተዳደር በማግኘታችን ነው ብለዋል ፡፡


