የድሬዳዋ አስተዳደር የ 2014 ዓ.ም የሁለተኛው ምእራፍ የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔትና ስራ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሀ-ግብሩ ላይ ለመታደም በርካታ እንግዶች ወደ ከተማችን ድሬዳዋ በመምጣት ላይ ይገኛሉ ።

    በዛሬው እለትም የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒን ጨምሮ ሌሎች ሚኒስትር ዲኤታዎች እንዲሁም ከፍተኛ አመራሮች ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር መንገድ ሲደርሱ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የአስተዳደሩ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል ።
    በነገው ዕለት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ከተማና መሠረተ ልማት ሚኒሰቴር ከድሬ ዳዋ አሰተዳደር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የከተሞች ልማታዊ ሴፍትኔት ስራ ፕሮጀክት /UPSNJP/ የአዲሱ ፕሮጀክት ትግበራ ማሰጀመሪያ ስነ ስርዓት በድሬዳዋ እንደሚከናወን የሚታወቅ ነው።