ድሬዳዋ ያፈራችው እውቁው የኦሮምኛ ቋንቋ ድምፃዊ ክቡር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ እንኳን በጤና አገናኘን።

    በዛሬው እለት የአስተዳደራች ከንቲባ አቶ ከዲር ጁሀር እና የድሬዳዋ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ የድሬዳዋውያን ምልክታችንና አምባሳደራችን የሆኑት ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ ቤት በመገኘት ከህክምና መልስ በሙሉ ጤና ላይ በመሆናቸው ደስታቸውን ገልጸዋል።
    የአስተዳደሩ ከንቲባ ድሬዳዋ ያፈራችው ኢትዮጵያዊው የኦሮምኛ ቋንቋ ድምፃዊ፤ ክቡር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ፤ ከማንም በላይ ለእኛ ለድሬዳዋውያን ምልክታችንና አምባሳደራችን ነው ብለዋል።
    አክለውም ደ/ር አሊ ቢራ በሄደበት ሁሉ የድሬ ስሟ ተነስቷል፣ በሙዚቃዎች ውስጥ ሰምተው የወደዷትን ድሬዳዋ ለማየት ብዙዎች የጓጉበት፣ ከርቀት መጥተው ሙቀቷንና ጣፋጭ ፍቅሯን የቀመሱ ተደስተው ሲመለሱ ሱስ የሆናባቸው እዚሁ የቀሩትም እጅግ በርካታ መሆናቸውን በጉብኝቱ ላይ አንስተዋል።