የፌደራል የከተማና መሰረተ ልማት ሚንስቴር የከተሞች ገቢ ሪፎርም ፕላን ጽህፈት ቤት ለአንድ ዓመት ሲያስጠናው የነበረው ልዩ ባህሪ ያላቸው ንብረቶች ልየታ ፣ በጂአይኤስ ካርታ ማስፈርና ግመታ የያዘውን ጥናት ሰነድ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒሰቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ለድሬዳ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሀር ዛሬ በ ኒው ብሎሶም ሆቴል በተከሄደ ስነስርዓት አስረክበዋል ፡፡
ከንቲባ ከዲር ጁሀር በርክክብ ስነስርዓቱ ባስተላለፉት መልዕክት አሁን የተረከብነው የጥናት ሰነድ ወደ ተግባር ሲገባ በአስተዳደራችን በንብረት ልየታና ግመታ ዘርፍ ያለው የአቅም ውስንነት ለማሻሻል ብሎም የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎታችንን ለማዘመን በምናደርገው ጥረት አይነተኛ አስተዋጽኦ አለው ያሉ ሲሆን ለህበረተሰቡም ንብረት ለማስገመት የሚደረገውን ምልልስ ትርጉም ባለው መልኩ የሚቀንስ ፤ ከፋይናንስ ተቋማት ለመበደር የሚያስችልና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የሚፈታ ነው ፡፡
ልዩ ባህሪ ያላቸው ንብረቶች ልየታ ፣ በጂአይኤስ ካርታ ማስፈርና ግመታ ፕሮጀክት ወደ አስተዳደራን የሚመጡ ባለሀብቶች ባለሀብቱ አዋጭ የኢንቨስትመንት ስትረቴጂ ለመቅረጽ አጋዥ ኃይል ስለሚሆናቸው ለአልሚዎች ካለው ጠቀሜታ ባለፈ የኢንቨስትመንቱን ዘርፍ ለማሳደግ ለምናደርገው ጥረት ስንቅ የሚሆን ነው ብለዋል ፡፡
የከተማና መሰረተ ልማት ሚንስቴር ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ሰነዱ ልዩ ባህሪ ያላቸው ንብረቶች ልየታ ፣ በጂአይኤስ ካርታ ማስፈርና ግመታ ከተሞች ከዚህ በጣራና በግድግዳ እየተባለ በዘልማድና በግምት የሚሰበሰበውን ግብር አስቀርቶ የከተሞችን ገቢ ማሳደግ እንደተጠበቀ ሆኖ ህዝቦች ላይ ጫና ለማድረስና የማይገባቸውን እንዲከፍሉ ሳይሆን በትክክልም ልዩ ባህሪ ያላቸው ተቋማት በትክክለኛው መንገድ ለገዢውም ለመንግስትም ፍትሀዊ በሆነ መንገድ እንዲተዳደርና በደላላ ይመራ የነበረው ገበያ ስርዓት ተበጅቶለት በስርዓት እንዲተዳደርና ሁሉም የሚገባውን ጥቅም እንዲያገኝ የሚረዳ ከሁሉም በላይ ሌብነትን ማስቀረት የሚያስችል ነው ብለዋል ፡፡
በጥናቱ በከተማ የሚገኙ ዘጠኙም ቀበሌዎች 1122 ንብቶች ልየታ ፣ በጂአይኤስ ካርታ ማስቀመጥና ግመታ እንደተሰራላቸው የገለጹት ጥናቱን ያጠናው ተቀባና ጓደኞቹ አማካሪድርጅት ባለቤትና ስራ አስኪያጅ አቶ ተቀባ የድሬዳዋ አስተዳደር ድጋ ባይጨመርበት ኖር ውቴታማ አንሆንም ነበር ብለዋል ፡፡
በጥናቱ የተካተቱት 1122 ልዩባህሪ ያላቸው ንበረቶች ጠቅላላ ግምትም 57,363,131,686,47 ( አምሳ ሰባት ቢሊየን ሶስት መቶ ስድሳ ሶስት ሚሊየን ስድስት መቶ ሰማንያ ስድስት ሺህከአርባ ሰባት መሆኑ በመድረኩ ተገጸዋል ፡፡


