በዛሬው እለት ሁለተኛው ምእራፍ የከተማ ልማታዊ ሴፍትኔትና ስራ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር የከተማ ልማትና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ\ሮ ጫልቱ ሳኒ ጨምሮ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ ፣ ሚኒስትር ዲኤታዎች ፣ ከፍተኛ የአስተዳደሩ አመራሮች ፣ የቋሚ ኮሚቴ አባላት ፣ የአለም ባንክ ተወካዮች ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች ተሳታፊ በሆኑበት በታላቅ ድምቀት መካሄዱ ይታወቃል ።
የዚሁ ፕሮግራም አንድ አካል የሆነውና የሀዲድ መስመር ዝርጋታ እ.ኢ.አ በ 1895 ዓ.ም ከመዘርጋቱ ጋር ተያይዞ ባቡር ወደ ድሬዳዋ ሲገባ የድሬዳዋ ምስረታም አንድ ላይ ሊመሰረት የቻለውና የከተማችን ድሬዳዋ ልዩ መገለጫ በሆነው ታሪካዊው ባቡር ላይ ጉብኝት ተካሂዷል ።
በዚሁም የባቡር ጉብኝት ላይም በሁለተኛው ምእራፍ የከተማ ልማታዊ ሴፍትኔትና ስራ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ላይ ተሳታፊ የነበሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በጉብኝቱ ላይ ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን በዚህ ታሪካዊ ባቡር ላይ ጉብኝት በማድረጋቸው በእጅጉ ደስተኛ መሆናቸውንም ተናግረዋል ።


