19ኛው የፅዳት ዘመቻ ሳምንት

    በ05 ቀበሌ በተካሄደው በዛሬው ዘመቻ የከተማ መሰረተ ልማት ሚንስትር ወሮ ጫልቱ ሳሊን ጨምሮ የድሬደዋ ምክትል ከንቲባ አቶ ሃርቢ ቡህ ና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ብድሬደዋ የሚገኙ 10ር የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች፣የፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች እና አባለት ተሳታፊ ሆነዋል።
    በወቅቱ የከተማ መሰረተ ልማት ሚንስትር ወሮ ጫልቱ ሳሊን ባደረጉት ንግግር ድሬደዋ የመቻቻል ከተማ መሆኗን ገልፀው ድሬዳ ላይ ያየነው የከተማዋን ፅዳት የማስጠበቅ ንቁ ስራ ለሌሎች ተምሳሌት የሚሆን ነው ሲሉ ተናግረዋል።
    በጋራተባብሮ አካባቢን የማልማቱ ስራ በሌሎች የልማት ዘርፎች በእኛነት መንፈስ መደገም አለበት ብለዋል ምኒስትሯ።
    የድዴደዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሃርቢ ቡህ በፅዳት ዘመቻው ድሬደዋን ውብ አረጓዴነት ለመመለስ በየሳምንቱ የፅዳት ዘመቻ እየተደረገ ነው።ጥዳቱ ከፍተኛ አመራሮች የመንግስት ሰራተኞች የየአካባቢው ነዋሪ ተሳታፊ እየሆነ ይገኛል ሲሉ ገልጸዋል።
    የፅዳት ስራው አካባቢን ንጥህና ከማስጠበ፨፨ ባለፈ ለጤና ያለው ፋይዳ የጎላ መሆኑ አቶ ሃርቢ አስረድተዋል።ዘመቻውን ህዝባዊ ለማድረችም ከፍተኛ አመራሩ በግንባር ቀደምትነት እየተሳተፈ ይዘልቃል ብለዋል።