በመርሀ-ግብሩ ላይም የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ፣ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ ፣ ሚኒስትር ዲኤታዎች ፣ ከፍተኛ የአስተዳደሩ አመራሮች ፣ የቋሚ ኮሚቴ አባላት ፣ የአለም ባንክ ተወካዮች ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፣ የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች እንዲሁም ባለ ድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል ።
ሁለተኛው ምእራፍ የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔትና ስራ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር በዛሬው እለት በሽንሌ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አዳራሽ በታላቅ ድምቀት እየተካሄደ ይገኛል ።


