ምዝገባውን ሳያካሂዱ ሚቀሩ ባለንብረቶች የድጎማው ተጠቃሚ እንደማይሆኑ ተጠቁሟል፡፡
መንግስት ከጊዜ ወደጊዜ እየናረ የመጣውን የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በመደጎም ገበያውን ለማረጋጋት ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡
ይሁንና ከቀጣዩ አመት ወዲህ ለህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ከሚሰጡ ተሸከርካሪዎች ውጭ ያሉት በመደበኛው የገበያወጋ እንዲገበያዩ ድጎማውን ሊያነሳ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ለዚህም ደግሞ በድሬደዋ የሚገኙ እና በህዝብ ትራንስንስፖርት ዘርፍ ለሚንቀሳቀሱ ባለንብረቶች እና ማህበራት በመንግስት የተዘጋጀው የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንዲመዘገቡ በተለያዩ መንገዶች ጥሪ ተላልፎ በኢትዮ ቴሌኮም በኩል ምዝገባ እየተካሄደ ቢገኝም ምዝገባው በሚፈለገው መጠን አለመሆኑን ተጠቁሟል፡፡
ይህን ያስታወቁት በትራንስፖርት እና ጂስቲክ ሚኒስቴር የድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ሰአዳ አዋሌ ናቸው፡፡
ዋና ዳይሬክተሯ ዛሬ ለሚዲያ በሰጡት ቃለመጠቅ እንደስታወቁት መንግስት ለህዝብ አገልግሎት ሚውሉ ተሽከርካሪዎችን ብቻ መደጎሙ ማህበረሰቡ በትራንስስፖርት መጨመር ላልተፈለገ ወጪ እንዳይዳርግ መሆኑን አውስተው በዚህም መሰረት ድጎማው ለህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች ብቻ መዘጋጀቱንና በዚሁ መሰረት እንደ አስተዳደርም ምዝገባውን በዋናው እና ከዚራ ቶታል ፊት ለፊት በሚገኘው በኢትዮ ቴሌኮም የሸያጭ ማዕከላት እንደሚከናወን የጠቆሙት፡፡
በዚህም ባለንብረቶች ዋና ወይም ቅጂ ሊብሬ እንዲሁም የታደሰ መታወቂያ በመያዝ የተሸከርካሪውን ባለቤት የስልክ ቁጥር በማሳወቅ የቴሌብር አገልግሎት ምዝገባ ከወዲሁ እንድያከናውኑ ወ/ሮ ሰአዳ ጥሪ አቅርበዋል ፡፡
በጥሪው መሰረት ምዝገባ ማያካሂደዱ ኋላ ለሚደርሰው መጉላላት ተቋሙ ኃላፊነት እንደማይወስድም የገለፁ ሲሆን በቀጣይ ድጎማው እንደ ተጀመረ ለሚወጣው ታሪፍም ተገዥ እንዲሆኑ ይደረጋልም ሲሉ አያይዘው ጠቁመዋል፡፡


