የማህበራዊው ሚዲያ የተጽእኖ ምህዳር ሰፊ ነው። ጥቅሙን እያገኘን ጎጂ ተጽእኖውን የምንቀንስበትን መንገድ መፈለግ ነው ያለብን። በማህበራዊ ሚዲያ ገቢ የሚያገኙ ሰዎች ከገቢው የተነሳ የሀስትና ጎጂ ዜናዎችን ይሰራሉ።
ይህ የሚስተካከልበት መንገድ መኖር አለበት። እነዚህ ማህበራዊ አንቂ የተሰኙ ሰዎች በጥፋት ተግባራት ላይም የሚሳተፉ ናቸው። ከለውጡ በኋላ የሚዲያ ብዝሃነት ጨምሯል። ጋዜጠኝነት የሚከበር ሙያ ነው፣ ከወሬ ፖለቲካ አልፎ በትጋት መሥራት ያስፈልጋል። ሀገር እያፈረሱ፣ በሀገር ሕልውና ላይ እየቆመሩ ሙያተኝነት የለም። ጋዜጠኝነት የወንጀል መደበቂያ ሳይሆን የሀሳብ ማፍለቂያና ማካፈያ መሆን አለበት።
የትኛውም አካል የተያዘው በሕግ ማስከበር ሥራ እንጂ በሌላው አይደለም። ሀገር የሚጠበቅ መከላከያን መስመር አልፎ መድፈርና ለመከፋፈል መሞከር ዋጋ ያስከፍላል። የሚሰራው ሥራ ሁሉ ለሀገር ደህንነት መሆኑ ታሳቢ መደረግ አለበት።


