በትግበራ ላይ የሚገኘውን የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ምክንያት በማድረግ በህዝብ ትራንስላይ መጉላላት ሚፈጥሩ የተሽከርካሪ ማህበራትንም ሆነ አለአግባብ ከታሪፍ በላይ ለመጫን ሚሞክሩ አሽከርካሪዎችን እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምር በትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ሚኒስቴር ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስታወቀ።

    በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ሚመራ ቡድን ድንገታዊ ምልከታን በህዝብ ትራንስፖርት ማህበራት እና በመናኸሪያዎች ላይ አድርጓል።
    መንግስት ለህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭ ባለንብረቶች በታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ ለማህበረሰቡ በተመጠጣነ ዋጋ አገልግሎት እንዲሰጡ ተሳቢ ያደረገ አሰራርን ዘርግቶ ወደትግበራ ገብቷል።
    ይህንኑ በማስመልከትም ከማደያ ባለነብረቶች አሽከርካሪዎች እና የተሽከርካሪ ባለንብረቶች በትግበራው ላይ በቂ መረጃን በመስጠት ሰኔ 29 የሙከራ ትግበራውን ጀምሯል። ይሁንና ይህን ክፍተት በመጠቀም አላግባብ ታሪፍ ለመጨመር እና ህዝብን ለእንግልት የዳረጉ የሀገር አቋራጭ የህዝብ ማመላለሻ ባለንብረቶችን እና ማህበራት እንደሁም አሽከርካሪዎችን በድንገተኛ ምልከታ በመለየት ከተግባራቸው ታቅበው ህዝብን ባግበቡ እንዲያገለግሉ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ወደመደበኛ አገልግሎታቸው እንዲገቡ ተደርጓል።
    ይህንኑ በማስመልከት በመናኸሪያዎች ላይ ድንገተኛ ጉብኝት በማድረግ አቅጣጫ ያስቀመጡት የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ሰአዳ አዋሌ መሰል ተግባራት ተቀባይነት የሌላቸው እና ማህበራትን ሆነ በተገልጋዩ እንግልት በሚፈጥሩ አሽከርካሪዎችን ለቅጣት ሚዳርግ ተግባር ሆኑን ገልፀው ችግሮች ካሉ መደበኛ ስራቸውን ሳያቋርጡ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በመቅረብ ጥያቄያቸውን በማቅብ መወያየት እንደሚችሉ ጠቁመው በመሰል ተግባር ላይ ያሉ ማህበራት ከተግባራቸው እንዲታቀቡ አሳስበዋል።
    በወቅቱም በድሬደዋ ምዝገባቸውን ላደረጉ ማህበራት እና ኮድ 3 አንድ የሆኑ የህዝብ ትራንስፖርት ላይ ለተሰማሩ ተሽከርካሪዎ የታለመለት ነዳጅ ድጎማ መለያ ስቲከር በየተሽከርካሪዎቹ ላይ ለጥፈዋል።