በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ ይወያያል።
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች 6ኛው ምክር ቤት በ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ በሚያካሂደው 16ኛ መደበኛ ጉባዔ፤ ሰሞኑን በተከሰተው የዜጎች የፀጥታ እና ደኅንነት ጉዳይ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚወያይ ይጠበቃል።
ምክር ቤቱ በተጨማሪም፤ በአዲሱ የ2015 የበጀት ድልድል ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቀው ይጠበቃል።
የብልጽግና ፓርቲ ሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት የምክር ቤቱን ስብሰባ የተመለከቱ መረጃዎች ከጥኋቱ 3:00 ጀምሮ ወደ እናንተ የሚያቀርብ ይሆናል፤ይከታተሉን።


