• የኢትዮጵያን የዳገት ጉዞ ከቻላችሁ ወደላይ ግፏት ደግፏት፤ ካልቻላችሁ ስሜት ካሸነፋችሁ ቢያንስ እንዳትንሸራተት ታኮ አስቀምጡላት፤ ጠላቶቻችን የሚፈልጉት ወደ ኋላ እንድትንሸራተት ነውና ያንን አታድርጉ፤
• ኢትዮጵያ ወደ ዳገት ጉዞ ላይ ነው ያለችው፤ብዙ ጉልበት፣አንድነት እና ትብብር ይጠይቃል፤
• የጠላቶቻችን ፍላጎት ወደ ኃላ መመለስ ነው፤የእነሱ ፍላጎት እንድንበታተን፣እንድንፈርስ እና እንድንጋጭ ነው፤
• የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች አክቲቪስቶች ግድያ ሲፈጸም አየሩን ይሞሉታል፤ ፖሊስ እርምጃ ሲወስድ ህጋዊ ነገር ሲከበር ግን የሉም፤
• አሸባሪው ሸኔ የኦሮሞ ህዝብ ቀንደኛ ጠላት ነው፤ ሸኔ ለማንም የማይመለሱ አውሬዎች ናቸው፤ ለምንድን ነው አውሬ የሆኑት የሚለው ጥናት ይፈልጋል፤ የፖለቲካ አላማ ግን የላቸውም፤
• የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች ቤተሰቦች ተገድለዋል፤ በመቶ የሚቆጠሩ አመራሮች ተገድለዋል፤ ይሄንን ጠላት የሁላችንም ጠላት ነው ብለን ከተነሳን እናጠፋዋለን፤
• ለሸኔ የሚራራ የሚያዝን የተለየ ስሜት የለንም፤ እንደ ሸኔ ያሉ ኃይሎች ዋና ፍላጎታቸው ፓርላማው ሚዲያው ዓለም ስለእነሱ እንዲያወራ ነው፤
• ሁሉም ኢትዮጵያዊ በእኩልነት የሚኖሩባት ኢትዮጵያን ለመመስረት ነው ፍላጎታችን እየሰራን ያለነወም ለዚያ ነው፤
• ጽንፈኞች በየትኛው ሰፈር ይደራጁ ሁለት መርዝ አላቸው፤ አንደኛው የእኔ ብቻ ጥሩ ነው የሚለው ነው፤ ሁለተኛው በጣም የበዛ የራስ ሀዘኔታ፤ የነገሮች ሁሉ ማዕከል ራስን ብቻ ማድረግ ነው፤
• ጽንፈኝነት ዓለምን አልጠቀመም፣ ኢትዮጵያን አይጠቅምም፤ መግረፍና ማፈን ከብልጽግና ጋር አብሮ አይሄድም፤


