ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ካነሷቸው ነጥቦች መካከል፦

    • የ11 ወራት የመንግስት ገቢ 309 ቢሊየን ብር ሲሆን፥ የእቅዱን 93 በመቶ ማሳካት ተችሏል።
    • ገቢው ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የዘንድሮው የ50 ቢሊየን ብር ጭማሪ አለው።
    • በተጓዳኝ መንግስት 500 ቢሊየን ብር በ11 ወራቱ ውስጥ ወጪ አድርጓል።
    • ከወጪው ውስጥ 100 ቢሊየን ብር ገደማ ማለትም 1 ነጥብ 7 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላሩ የእዳ ክፍያ ነው።
    • የወጭ ምርት ላይ ያለው እምርታ በጣም በጣም ግዙፍ ነው። ይህንን ለጥቂት አመታት ጠብቀን ማስቀጠል ከቻልን የወጭ ና ገቢ ሚዛንን ለማስጠበቅ እና የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ለመፍታት ትልቅ አስተዋጽኦ አለው።
    • ኢትዮጵያ በ2002 አመተ ምህረት 2 ቢሊየን ዶላር ኤክስፖርት አድርጋ ነበር። ከ2002 እስከ 2012 ድረስ ሶስት ቢሊየን ዶላር ለማድረስ ትንገታገት ነበር። በአስር አመት ውስጥ አንድ ቢሊየን ነው የጨመርነው።
    • ባለፉት ሁለት አመታት በሰራነው ስራ ግን በሁለት አመት ውስጥ ከአንድ ቢሊየን በላይ በመጨመር በሸቀጦች የወፅ ምርት ከአራት ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል። በአገልግሎት ደግሞ በ25 % አድጎ ከ ስድስት ቢሊየን ዶላር በላይ አግኝተናል።
    • ከዚህ ውስጥ ቡና በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር ገቢ ያስገኘ ሲሆን፥ ይህን ስኬት በሻይ፣ በአትክልት እና ፍራፍሬ ማስፋት ከተቻለ ከፍተኛ ገቢ ማግኘት ይቻላል።
    • ቀጥተኛ የወጭ ኢንቨስትመንት ፍሰት ሲታይ የ10 በመቶ እድገት በማሳየት ከ3 ቢሊየን ዶላር በላይ ተገኝቷል።
    • የፋይናንስ ዘርፉ በተወሰዱ የሪፎርም ስራዎች ከፍተኛ እድገት ያስመዘገበ ሲሆን፥ በአሁኑ ወቅት የባንኮች አጠቃላይ ሀብት 2 ነጥብ 3 ትርሊየን ብር ደርሷል።
    • ባንኮቹም 353 ቢሊየን ብር ብድርም አቅርበዋል።
    • በግብርናው መስክ በተለይ በኩታ ገጠም እርሻ እምርታ ተገኝቷል።
    • በዚህም ምክንያት ሀገሪቱ በሚቀጥለው ዓመት ስንዴን ወደ ውጭ መላክ ትጀምራለች። ይህን ለማሳካትም ሰፋፊ ስራ እየተከናወነ ይገኛል።