ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የንፁሃን ዜጎች ሕይወት መቀጠፍን በተመለከተ ካነሷቸው ነጥቦች መካከል

    • እነዚህ ዜጎች ባልሰሩት ወንጀል ፣ በማያውቁት ጉዳይ በገዛ ሀገራቸው እና ቀያቸው ህይወታቸውን ለማሻሻል ደፋ ቀና ሲሉ ባልተገባ መንገድ ህይወታቸውን የሚቀጥፉ ገዳዮች አጥፊ ስብስቦች ያደረሱባቸው ጥቃት በእጅጉ የሚያሳዝን ከመሆኑ ባሻገር ህይወታቸውን ለመታደግ ባለመቻላችን እንደ ሀገር እንደ መንግስት እንደ ህዝብ ጥልቅ ሀዘን ይሰማናል።
    • የንፁሃንን ደም በከንቱ የሚያፈሱ የትኛውም ሸኔም ይሁን ሌሎች የጥፋት ኃይሎች መጥፋታቸው የማይቀር ነው፤ ማሸበር ይችሉ ይሆናል እንጂ ከዋና ዓላማችን አያስቀሩንም፤
    • መንግስት 24 ሰዓት የዜጎች ህይወት ለመታደግ ከፍተኛ ስራ እያከናወነ ይገኛል፤ ከዚህ ውስጥ ያመለጠ እንዳለ ሆኖ። በዚህ ውስጥ መስዋዕት የሚሆኑ የፀጥታ አካላት፣ ወታደሮች እና የክልል ልዩ ሀይሎች ህይወታቸውን ገብረው እየጠበቁ ነው።
    • ሽብር አሁን ባለው ሁኔታ የጠቅላላ የዓለም ሁሉ ፈተና ነው። ለኢትዮጵያ ተለይቶ የተሰጠ አድርገን ማሰብ የለብንም።