• በግፍ ህይወታቸውን ላጡ ለተገደሉ ንፁሀን ዜጎች የሚሰማኝን ጥልቅ ኃዘን መግለፅ እፈልጋለሁ፤
• ባልሰሩት ወንጀል በማይመለከታቸው ጉዳይ ባልተገባ መንገድ ህይወታቸውን ለሚቀጥፉ ገዳዮች አጥፊ ስብስቦች በእጅጉ ዜጎቻችንን ህይወታቸውን መታደግ ባመቻላችን ጥልቅ ሃዘን ይሰማናል፤
• አሁን እየደረሰ ያለው ችግር መንግስት ተገቢውን ትኩረት ስላልሰጠ አይደለም፤በርካታ የፀጥታ አካላት ህዝቡን ከጠላት ለመጠበቅ ሲሉ መስዋዕትነት ከፍለዋል፣እየከፈሉም ይገኛሉ፤
• ሸኔ እና ሌሎች የሽብር ቡድኖች የራሳቸው እግር የላቸውም፤
• የትኛውም ስብስብ ሸኔም ይሁን ሌላ አሸባሪ ሀይል በጀመርነው መንገድ ጉዟችንን አጠናክረን የምንቀጥል ከሆነ ይጠፋሉ። አላማ የላቸውም፣ ግብ የላቸውም እሳቤያቸው ጥፋት ስለሆነ የእኛን ጉዞ ማደናቀፍ አይችሉም፤ መፈተን ይችላሉ ፈትነዋል ግን ማሸነፍ አይችሉም፤
• መንግስት ህዝብን የማድመጥ ቀዳሚ ተግባሩ ነው፤ እውነት ነው፤ ህዝብም የመረጠውን መንግስት የማድመጥና የማገዝ ቀዳሚ ተግባሩ ነው፤
• ንጹሃን ዜጎችን ማጥቃት፣አገርን ለማተራመስ መስራት የሽብር ቡድኖች ዓላማ ነው፤
• ከሳሽ እና ጠያቂ ብቻ ሳይሆን ኃላፊነት ወስዶ አገራቸውን ለመታደግ ከመንግስት ጋር ተሰናስለው መስራት ይጠበቅባቸዋል


