በናፍቆት የድሬዳዋ ሳምንት የደም-ልገሳና የህፃናት መዝናኛ መርሀ-ግብሮች ተካሄደ ።

    በድሬዳዋ አስተዳደር ከሀምሌ 11 እስከ ሀምሌ 16 2014 ዓ.ም ድረስ ናፍቆት የድሬዳዋ ሳምንት በተለያዩ መርሀ-ግብሮች በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ሲሆን በዛሬው እለትም ልጆችንና ቤተሰቦችን አሳታፊ ያደረጉ የተለያዩ መርሀ-ግብሮች ከመካሄዳቸውም በዘለለ የደም ልገሳ ፕሮግራምም ተካሂዷል ።
    በነዚህም መርሀ-ግብሮች ላይ ተሳታፊ የሆኑ አካላት በበኩላቸው በናፍቆት የድሬዳዋ ሳምንት ላይ በሚካሄዱት ፕሮግራሞች ላይ በመሳተፋቸው ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረው በቀጣይም እንደዚህ አይነት አዝናኝና አስተማሪ የሆኑ ፕሮግራሞች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም ነው የተናገሩት ።
    ከምንም በላይ ደም በመለገስ በደም እጦት ምክንያት ህይወታቸውን የሚያጡ ዜጎችን መታደግ እንደሚገባ በናፍቆት የድሬዳዋ ሳምንት ላይ የደም ልገሳ ሲያደርጉ ያገኘናቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረው ይህም ተግባር ለአንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በቀጣይም በአካባቢያቸው ያሉትን የህብረተሰብ ክፍሎች በማስተባበር ደም እንደሚለግሱም ተናግረዋል ።
    ናፍቆት የድሬዳዋ ሳምንት በነገው እለትም የሚቀጥል ሲሆን የምስጋናና የሽልማት ቀን መርሀ-ግብር የሚካሄድ ይሆናል ።