የመሬት ልማትና ማኔጀመንት ቢሮ በ2015 በጀት አመት ህገወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከል ትኩረት ሊሠጥበት እንደሚገባ ተገለጸ። ቢሮው የ2014 እቅድ የአፈጻጸም ሪፖርት እና የ2015 በጀት አመት እቅዱን በህዝብ ክንፍ አስገምግሟል።

    በመድረኩም ከአስተዳደሩ የተውጣጡ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የተሳተፋ ሲሆን የአፈጻጸም ሪፖርትና እቅድ ቀርቦ ሠፊው ውይይት ተካሂዷል።
    ከመድረኩም ቢሮው እያከናወነ በሚገኘው የሪፎርም ስራ እያመጣ ያለው ለውጥ አበረታች መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን በቀጣይም የተቋቋመለትን አላማ ከዳር ለማድረስና የህብረተሰቡን ቅሬታው ከመቀነስ አኳያ ይበልጥ መንቀሳቀስ እንደሚገባ ተመላክቷል።
    በተጨማሪም መረጃን ከኢንፎርሜሽን ኮምንኬሽን ቴክኖሎጂና ጋር ለማስተሳሰር እየተከናወነ የሚገኘው ተግባር ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገልጿል።
    እንዲሁም ህገወጥ የመሬት ወረራን አስቀድሞ ከመከላከል አንጻር ይበልጥ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ተጠቅሷል። ቢሮው ወደ ቀበሌው በመውረድ በቅርበት መስራት እንደሚገባውና ይህም በቢሮው ላይ በስፋት የሚነሱ ቅሬታዎችን፣ ህገወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከል የሚያስችል በመሆኑ ትኩረት ሊደረግበት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
    ከልማት ተነሺዎች ጋር በተያያዘም ከካሳ ክፍያ እና ምትክ ቦታ ከመስጠት ባለፈ ተነሺዎች የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብርና ተጠቃሚነታቸው ለማረጋገጥ የሚያስችል አሠራር ለመዘርጋት ቢታሰብበት የሚል አስተያየትም ተነስቷል።
    በተጨማሪም ቢሮው ሙስናና ኪራይ ሰብሰባቢነትን ከመከላከል አኳያ፣ ከሰው ሃብት ልማት አንጻር እንዲሁም ከተቋሙ ጋር በቅርበት የሚሰሩ ተቋማት ስልጠናዋች መስጠት እንዲሁም የገጽታ ግንባታ ስራ ላይ ትኩረት ቢያደርግ የሚሉ አስተያየቶች ተሰጥተዋል።
    በመድረኩ ለተነሱ አስተያየቶችና ጥቆማዎች የስራ ክፍል ኃላፊዎችን ምላሽ ሰጥተውበታል። መድረኩ ቢሮ ኃላፊና ምክትል ቢሮ ኃላፊ የተመራ ሲሆን የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ መሃመድ አብዱላሂ ከመድረኩ የተነሱ ሃሳቦች በግብአትትነት በመጠቀም እቅዱን በማዳበር በበጀት አመቱ የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ቢሮው ይንቀሳቀሳል ብለዋል።
    የቢሮው ኃላፊ ኢንጂነር ሳጂድ አሊይ በበኩላቸው ቢሮው በሪፎርሙ የተጀመሩ ስራዎች በ2015 በጀት አመት የሚቀጥል በመሆኑ ከመድረኩ የተነሱ ሃሳቦችን በማካተት የተሻለ አገልግሎት ለነዋሪው ለማቅረብ ጥረት ይደረጋልም ብለዋል።