አስተዳደሩ በገነባቸው የልማት ፕሮጀክቶች ውስጥ የትምህርት ቢሮ የአሰሊሶ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤትንና የመድሀኒዓለምን አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታ ሙሉ ለሙሉ መጠናቀቁንየድሬደዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሐላፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ ገለፁ፡፡ አሰሊሶ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 20 መማሪ ክፍሎች ሲኖሩት ሁለት ባለ 6 ቀዳዳ ሽንት ቤት፣ 1 ባለ 4 ቀዳዳ ሽንት ቤት እንዲሁም አጥርና የጥበቃ ቤት የያዘ መሆኑን ሃላፊዋ ተናግረዋል፡፡ በዚህም በ2015 የትምህርት ዘመን ትምህርት መስጠት ሲጀምር 1000 ተማሪዎችን የመቀበል አቅም ሲኖረው ይህም በአካባቢው ላሉ ሶስት ቀበሌዎች ማለትም ለሁላሁሉ፣ ለአሰሊሶና ለገዳንሰር ነዋሪዎች አገልግሎት ይሰጣል፡፡
ይህም ህብረተሰቡ ላይ ይደርስ የነበረውን አላግባብ ወጪና እንግልት ይቀንሳል ሲሉ ሀላፊዋ ተናግረዋል፡፡
የፕሮጀክቱ ግንባታ ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ሲሆን 121 ለሚሆኑ ዜጎችም ቋሚ እና ጊዜያዊ የስራ እድል መፍጠሩም ተናግረዋል፡፡ ሀላፊዋ አያይዘውም የመድሀኒአለም አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የግንባታ ፕሮጀክትም መተናቀቁን አንስተዋል፡፡በዚህም ትምህርት ቤቱ ከአንደኛ እስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል ድረስ ትምህርት እንደመስጠቱ ከፍተኛ የሆነ ጥበት መኖሩን አንስተወው በዚህ ፕሮጀክትም ይህንን ለመቅረፍ G+1 የነበረውን ወደ G+3 የማስፋፋት ስራ መሰራቱን ገልፀዋል፡፡
በዚህም 8 መማሪያ ክፍሎች ተገንብተዋል:: ይህ ደግሞ 800 የሚሆኑ ተማሪዎችን ማስተናገድ የሚችል ነዉ ፡፡ ለዚህ ፕሮጀክትም በአጠቃላይ ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገ ሲሆን ለ90 ሰዉ የስራ እድል ተፈጥሯል፡፡
ሀላፊዋ ፕሮጀክቶቹ በፍጥነትና በጥራት ከተያዘላቸው ጊዜ ቀድመው መጠናቀቃቸውን አንስተዋል፡፡ ለዚህም ከጎናቸው በመሆን አብረዋቸው የሰሩትንም አመስግነዋል፡፡
በመጨረሻም ወ/ሮ ሙሉካ የትምህርት ስራ የአንድ ሴክተር ስራ ባለመሆኑ ሁሉም ከጎናችን ቆመው ሊሰሩ ይገባል ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋ፡፡


