በተቋማትና በበጎ ፍቃደኛ ግለሰቦች የጋራ ትብብር የልማት ስራዎች እንዲሰሩ አስተዋፆ ላበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦች እውቅና ተሰጠ ።

    በድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት ህንፃ የባለጉዳይና የሰራተኞች መፀዳጃ ሽንት ቤትን የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊ ቴክኒክና ሞያ ኮሌጅ ከ 800 ሺህ ብር በላይ በሆነ ወጪ ሙሉ እድሳት ያደረጉ ሲሆን የድሬዳዋ አስተዳደር የፅዳትና ውበት ኤጀንሲና የአስተዳደሩ የውበትና አረንጓዴ ልማት ዳይሬክቶሬት ደግሞ ከ 380 ሺህ ብር በላይ በሆነ ወጪ የግቢውን ውስጣዊና ውጫዊ ክፍል በችግኝ አበባዎች ከማስዋብ በዘለለ የአጥሩን ዙሪያውን የብረት ቀለም በመቀባት ማስዋብ ችለዋል ።
    በአስተዳደሩ ከንቲባ ፅህፈት ቤት ህንፃ ከ 1 ነጥብ 1 ሚልዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለተሰሩት የልማት ስራዎች መሳካት ከፍተኛ አስተዋፆ ላበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦች በዛሬው እለት የእውቅና መርሀ-ግብር ተካሂዷል በዚህም መርሀ-ግብር ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፍት ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ሀላፊ የሆኑት አቶ ገበየሁ ጥላሁን የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊ ቴክኒክና ሞያ ኮሌጅ የመፀዳጃ ሽንት ቤቱን በዘመናዊ መልኩ በማደስ እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር ፅዳትና ውበት ኤጀንሲና የአስተዳደሩ የውበትና አረንጓዴ ልማት ዳይሬክቶሬት ደግሞ ግቢውን የማስዋብና የአረንጓዴ ልማት ስራዎች እንዲሰሩ በማድረጋቸው አመስግነው ተጠቃሚዎችም በሀላፊነት ሊንከባከቧቸውና ሊጠብቋቸው እንደሚገባም ነው አቶ ገበየሁ ጥላሁን በእለቱ የተናገሩት ።
    በድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት ህንፃ የግቢውን ውስጣዊና ውጫዊ ክፍል በችግኝ አበባዎች ከማስዋብ ባለፈ የአጥሩን ዙሪያውን የብረት ቀለም መቀባትና ማስዋብ መቻሉን የድሬዳዋ አስተዳደር ፅዳትና ውበት ኤጀንሲ ሀላፊ የሆኑት አቶ ሀቢብ ፋራህ እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር የፅዳትና ውበት ኤጀንሲ የውበትና አረንጓዴ ልማት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሸምሱዲን መሀመድ ተናግረው ወደ ህንፃው የሚመጡ ባለጉዳዮችና ሰራተኞችም የተሰሩትን የልማት ስራዎች በአግባቡ በመጠቀም ሊንከባከቧቸው እንደሚገባም ተናግረዋል ።
    የከንቲባ ፅህፈት ቤት የእቅድና ፕሮግራም ባለሞያ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ፀጋዬ ስራውን በማስተባበር ረገድ ላደረጉት አስተዋፆ እንዲሁም በችግኝ ንግድ ላይ የተሰማሩት አቶ ሀምሳሉ ደሴ በግል ተነሳሽነት የተለያዩ የአበባ ችግኞችን በነፃ በማቅረብ ላደረጉት አስተዋፆ ምስጋና ተችሯቸዋል ።
    በከንቲባ ፅህፈት ቤት ህንፃ ለተሰሩት የልማት ስራዎች መሳካት አስተዋፆ ላበረከቱ አካላት ከአቶ ገበየሁ ጥላሁን እጅ የእውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ።