የማህብረሰቡን ጤና በመጠበቅ እና አገልግሎቱን በጥራት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የድሬደዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ለምለም ገለጽ፡፡
የጤና አገልግሎት ጥራትን ለማጎልበትና ተደራሽነትን ይበልጥ ለማረጋገጥ በአስተዳደሩ 5 የጤና አገልግሎት የሚሰጡ የግንባታ ፕሮጀክቶች ከ70 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ መጠናቀቃቸውን ሀላፊዋ አስረድተዋል፡፡
የፕሮጀክቶች ወጪ በድሬደዋ አስተዳደር እና ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በጋራ የተሸፈኑ ናቸው ተብሏል፡፡
የጤና አገልግሎት ሰጪ የግንባታ ፕሮጀክቶችም ፤ የኢንዱስትሪ መንደር ጤና ጣቢያ ግንባታ፣በድልጮራ ሆስፒታል የሲቲ ስካን አገልግልት መስጫ ህንጻ ግንባታ እና የሲቲ ስካን ማሽን ግዢ ፣የማህበረሰብ መድሀኒት ቤት ግንባታ፣ የ4 ጤና ጣቢያ ኬላዎች ማስፋፊያ ሁለተኛ ትውልድ የገጠር ጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ትግበራ ለማጠናከር የሚከናወን የግንባታ ፕሮጀክት እንዲሁም የቢዮአዋሌ ጤና ጣቢያ እድሳት ና አነስተኛ የቀዶ ጥገና ማእከል ግንባታ ፕሮጀክቶች ሲሆኑ ሁሉም በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ግንባታቸው ሙሉ ለሙሉ ተጠናቀው ለአገልግሎት መዘጋጀታቸው ተገልጿል፡፡
የጤና ጣቢያ የግንባታ ፕሮጀክቶች በከተማ እና በገጠር ከ60 ሺ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑ ተነግሯል፡፡ፕሮጀክቱ በሚተገበርበት ወቅት እና ከተጠናቀቀ በኋላ ለ514 ዜጎች ቋሚ እና ጊዜያዊ እድል ተፈጥሯል ብለዋል፡፡
የግንባታ ፕሮጀክቱ የጤና አገልግሎት ጥራት በማሻሻል የማህበረሰቡን የጤና እንከኖች ሳይገጥሙ አስቀድሞ የመከላከል እና የመቆጣጠር ደረጃ በማሳደግ ረገድ ጉልህ ድርሻ ያላቸው መሆኑን የጤና ቢሮ ሀላፊ አስረድተዋል፡፡


