በአስተዳደሩ ደረጃውን የጠበቀ የካይዘን ኢኒስቲትዩት ህንጻ ግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ፡፡

    ፕሮጀክቱ በምስራቅ አፍሪካ ደረጃውን የጠበቀ የልህቀት ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ነው የተነገረው፡፡
    የፕሮጀክቱ ተግበራ በ01 ቀበሌ በመልካ ጀብዱ ሲሆን በ2009 ዓ.ም አሼቶ የተባለ የኮንስትራክሽን ድርጅት ጋር ውል ተፈጽሞ ፕሮጀክቱ መጀመሩ እና በተለያዩ ምክኒያቶች በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ማጠናቀቅ አለመቻሉን ነው የስራ አመራር ናካይዘን ኢንሰቲትዩት ሀላፊ አቶ አወቀ ለገሰ የገለጹት፡፡
    በዋናነት የፕሮጀክቱ መዘግየት የተፈጠረው፤በወቅቱ በነበረው የጸጥታ ችግር፣የዲዛይን ለውጥ፣የዋጋ ግሽበት አንዲሁም አማካሪ ድርጅቱ የክትትል እና የቁጥጥር ስራው በአግባቡ ያለመፈጸም ችግሮች መሆናቸውን ሃላፊው አንስተዋል፡፡
    የግንባታ ፕሮጀክቱ ከ170 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎ የተሰራው የልህቀት ማዕከል የተለያዩ ችግር ፈቺ የሆኑ ጥናቶችን እና ምርምሮችን ስልጠናዎችን በማድረግ፤ብቁ ተመራማሪ ዜጋን በመፍጠር ምርት እና ምረታማነትን በማሳደግ በኩል የኢንስቲትዩት ግንባታ አይነተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም 5.5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎ ለኢንስቲትዩት የግብአት መሳሪያ ግዢ መፈጸሙንም ሀላፊው ተናግረዋል፡፡
    ፕሮጀክቱ ከ150 በላይ ዜጎች ቋሚ እና ጊዜያዊ የስራ እድል መፍጠሩም አንስተው በቀጣይ ተቋሙ ስራ ሲጀምር ለ500 ዜጎች ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ፣ባለሙያዎች ቋሚ የስራ እድል እንደሚፈጥር ተነግሯል፡፡
    የካይዘን ስራ አመራር ፍልስፍና ተግባራዊ ማድረግ በተለይም ድሬደዋ የኢንዱስትሪ ቀጠና ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስተሪውን ምርትን እና ምርታማናትን በጥራት በማሳደግ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ሃላፊው አስረድተዋል፡፡
    የካይዘን አመራር ሳይንሳዊ አሰራርን በተቋሞች ተግባራዊ በማድረግ በአስተዳደሩ ከ15 ሚሊዩን ብር ከወጪና ከብክነት ለማዳን እንዳስቻላቸው ሀላፊው አስታውቀዋል።