የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታልን የድሬዳዋ ተወላጆችና ወዳጆች ጎበኙ ።

    በድሬዳዋ አስተዳደር ብሎም በአጎራባች ክልሎች ላይ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ከፍተኛ የሆነ የህክምና አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ እ.ኢ.አ በ 2002 ዓ.ም ግንባታው የተጀመረው የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል በተለያዩ ምክንያቶች ግንባታው መጓተቱ ይታወቃል ።
    ይህንንም ሪፈራል ሆስፒታል የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ተረክቦ ቀሪ ግንባታዎችን እያካሄደ ሲሆን በዛሬው እለትም ሪፈራል ሆስፒታሉን የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ኡባህ አደምን ጨምሮ ከፍተኛ የአስተዳደሩና የዩኒቨርሲቲው አመራሮች እንዲሁም የድሬዳዋ ተወላጆችና ወዳጆች ጎብኝተውታል ።
    ከጉብኝቷ በኋላም በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ቅጥር ጊቢ ውስጥም የአረንጓዴ ልማት የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብርንም አካሂደዋል።