የድሬዳዋ አሰተዳደር የ ንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ በከተማችን የሚስተዋለውን የኑሮ ዉድነት በዓልን ምክንያት በማድረግ ሰዉ ሰራሽ የኑሮ ዉድነት እንዳይከሰት ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንድቻል ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርገዋል።
የድሬዳዋ አሰተዳደር ም/ከንቲባ እና የንግድ እንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ሀርቢ ቡህ በዉይይት መድረኩ እንደገለፃ በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ለማስቆም ተቀናጅተው በመስራት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።
ህብረሰቡም አላሰፈላጊ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ስግብግብ ነጋዴዎችን በመቆጣጠር ህደት ዉስጥ የበኩሉንሚና እንዲጫወት ክቡር ምክትል ከንቲባዉ አሳስበዋል።


