በ2015 በጀት አመት በአስተዳደሩ የገጠር ክላስተሮች የሚገኙ የመንግስት ተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ የተሻለ ለማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለፀ።

    በድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አዘጋጅነት በ2015 በጀት አመት በአስተዳደሩ የገጠር ክላስተሮች የሚገኙ የመንግስት ተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ የተሻለ ለማድረግ በሚቻልበት አግባብ ከአራቱም የገጠር ክላስተር አመራሮች ጋር ውይይት ተደርጓል።
    በመንግስት የተቀረፁ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን በሚፈለገው ፍጥነትና የጥራት ደረጃ ተግባራዊ ለማድረግ እና በአስተዳደራች ውጤታማ የሆነ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ውጤቶችን ለማስመዝገብ የሚያስችለውን ሁለንተናዊ የማስፈፀም አቅምን የማጠናከር ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡
    በዚህም ብቃት ያለው የሰው ሃይል፣ የጠራ አደረጃጃት እና አሰራር ለመፍጠር አመራሩና የመንግሥት ሠራተኛው ቅልጥፍና እና ውጤታማነትን ማረጋገጥ የሚያስችሉ አዳዲስ አሠራሮችን ለመተግበር እና በሪብራንዲንግ እሳቤ የሲቪል ሰርቪሱን የደበዘዘ ገፅታ ለማደስ የሪፎርም ፕሮግራሞችን እንደ ሴክቶሬቹ ተጨባጭ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ተይዘው እየተሰራ ሲሆን በዚሁ አግባብ የገጠር ክላስተሮችንም ውጤታማ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል።
    በውይይቱም የገጠር ክላስተሮችን አገልግሎት አሰጣጥ ሪብራንድ ለማድረግ በ2015 በጀት ዓመት በሰው ሃብት ልማትና አስተዳደር፣ በለውጥና መልካም አስተዳደር፣ በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ እንዲሁም በሥራ አመራር ልማት እና በጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ ዘርፍ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ በሚቻልበት አግባብ ከአመራሮቹ ጋር ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን አገልግሎት አሰጣጥን የተሻለ ለማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው ሊሰሩ እንደሚገባም የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል ፡፡
    መረጃዉን የ ብሊክ ሰርቪስና ሰዉ ሀብት ልማት ቢሮ
    ኮሙኒኬሽን ክፍል ነዉ ያደረሰን