የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የልዑካን ቡድናቸው ድሬዳዋን እየጎበኙ ነዉ።

    በፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ በመገኘት ምልከታ ያደረጉ ሲሆን በአስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ስር የሚገኙትን የማሪያም ሰፈር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የሳቢያን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል
    የጉብኝታቸውም አላማም የተማሪዎች ምዝገባ ያለበትን ሁኔታ ለመመልከት እና የ2015ዓም የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማሩን ስራ በተሳካ መልኩ ለማስኬድ በአስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ በኩል እየተደረገ ያለውን የዝግጅት ምዕራፍ ስራዎች ምን ደረጃ ላይ እንዳሉ ለመገምገም መሆኑን በጉብኝቱ ወቅት ሚኒስተሩ ገልፀዋል ፡፡
    በቢሮዉ አጠቃላይ የትምህርት ሴክተር የዝግጅት ምዕራፍ ያለበት ደረጃ የሚያሳይ ማብራሪያ ቀርቦ ዉይይት ተደርጎበታል ።