“ለሀገር ክብር ለክብር እናብር” በሚል መሪ ቃል በድሬደዋ አስተዳደር የተለያዩ ቀበሌ ነዋሪዎች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሂዷል።
በኢትዮ-ጣሊያን ቴክኒክና ሞያ ኮሌጅ አዳራሽ የተካሄደው ውይይት የመነሻ ፅሁፉ የድሬደዋ አስተዳደር የግብርና መዕድና ኢነርጂ ቢሮ ሀላፊ አቶ ኑረዲን አብደላ ቀርቧል።
በውይይት መነሻ ፅሁፉ መንግስት በኢትዮጵያ የተከሰተውን ችግር በሰላም አማራጭ ለመፍታት በሩ ክፍት መሆኑንና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለመወያየት ቁርጠኛ መሆኑን በተደጋጋሚ በመግለፅ ላይ ይገኛል
ብለዋል።
ሆኖም አሸባሪው ህወሓት የተሰጠውን የሰላም እድል ከመጠቀም ይልቅ በተለያዩ ግንባሮች ጦርነት በመክፈት ያለ ግጭት መኖር እንደማይችል በተግባር እያሳየ ነው ብለዋል፡፡
በመድረኩ ነዋሪዎቹ በሰጡት አስተያየት “ለመከላከያ ለሰራዊታችን አስፈላጊውን ድጋፍ እናደርጋለን፤ ኢትዮጵያ በማንም አትፈርስም፤ እንደከዚህ ቀደሙ የአሸባሪዎችን ሀይል ለመጨረሻ ጊዜ እንቀብረዋለን ” ያሉት የቀበሌ 01 ነዋሪ የሆኑት አቶ ታደሰ ገቀባ ናቸው።
የ03 ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ሽመልስ እንዳሉት አሸባሪው ቡድን ለሶስተኛ ጊዜ በሀገራችን ላይ ጦርነት ከፍቷል ይህንን ያደረገው ህዝቡንና ሀገርን ሊመራ እንደማይችል እያወቀ ከጠላቶቻችን ጋር በመሆን ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ነው፤ ይህንን ደግሞ አንታገስም ብለዋል።
ሌላው አስተያየት ሰጪ አቶ አህመድ መሀመድ “የትግራይ ህዝብ በቁሙ እስር ላይ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን ልንደርስለት ይገባል” ብለዋል ።
በአሁኑ ወቅት የአሸባሪውን ቡድን የሀሰት መረጃ በማሰራጨት ህዝብ ለማወናበድ የሚሰሩ አካላትን በንቃት በመከታተል ለፀጥታ ሃይሎች አጋልጦ መስጠት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡


