በክብርት አፈ-ጉባዔ ወ/ሮ ፈቲያ አደን የተመራው የ07፤ የ08 እና የ09 ቀበሌ ነዋሪዎች ዉይይት መድረክ ዛሬ ነህሴ 29/2014 ዓ.ም የተካሄደ ሲሆን ለዉይይቱ የመነሻ ሀሳብ የሚሆን ሰነድ በድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ምክትል ሀላፊ የሆኑት በአቶ ደራራ ኢብራሂም ቀርቧል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የቀበሌዎቹ ነዋሪዎች በሰነዱ ላይ ሃሳብ አሰተያየት የሰጡ ሲሆን ይሄ ሀይል እራሱ ጠፍቶ ኢትዮጵያን ለማጥፋት የተዘጋጀ ሃይል በመሆኑ ሁሉም በአንድነት ይህን የጥፋት ሃይል ለማጥፋት ከመቸዉም ጊዜ በበለጠ መተባበርና በአንድነት መቆም እንዳለበት በመግለጽ መንግስት የሀገራችንን ሰላም ለማረጋገጥ የሚያደርገዉን ጥረት የሚደግፉ መሆኑን አረጋግጠዋል።
በዉይይቱ ማጠቃለያ ክብርት ወ/ሮ ፈቲያ አደን ሀገራችን የያዘችዉን የልማትና የብልጽግና ጎዳና ለማደናቀፍ ይህ የጥፋት ሃይል ለ3ኛ ጊዜ ያለዉን እሰትንፋስ ሁሉ በማሰባሰብ የሚያደርገዉ መፍጨርጨር መቼም ቢሆን የማይሳካ ህልም መሆኑን ገለጸዉ ይህን የጥፋት ሃይል ግብአተ መሬት ለማፋጠን ሁሉም በአንድነት መቆም እንዳለበት ጥሪ አቅርበዋል።


