አሸባሪው ህወሓት በሕዝብ ስም ወደ ትግራይ የሚገባውን እህል ለታጣቂዎቹ ብቻ እንደሚያቀርብ ዳግም ተጋለጠ

    አሸባሪው ህወሓት በሕዝብ ስም ወደ ትግራይ ክልል የሚገባውን እህል ለታጣቂዎቹ ብቻ እንደሚያቀርብ ዳግም ተጋልጧል።
    አሸባሪው ኃይል በሕዝብ ስም ወደ ትግራይ የሚገባውን እህል ችግር ላይ ከሚገኘው ሕዝብ ቀምቶ ለታጣቂዎቹ ብቻ እንደሚያቀርብ የተጋለጠው ከሰሞኑ በመከላከያ ሠራዊት በተደረመሰው ምሽግ ውስጥ ነው።
    አሸባሪው ህወሓት በምሽጉ ውስጥ የዕርዳታ እህል እና ሌሎች የምግብ አቅርቦቶችን ከዝኖ ለታጣቂዎቹ እንደሚያቀርብ ያረጋገጠ መሆኑን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
    የሽብር ቡድኑ ሌብነት እና አጭበርባሪነት በመከላከያ ሠራዊት የጀግንነት ተጋድሎ በተደጋጋሚ እየተጋለጠ ነው።
    EBC ነዉ የዘገበዉ