በቀጣይ ቀናትም በጎርፍና ቤት መደርመስ አደጋ፤ በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል። ጉዳት የደረሰባቸውን መሰረተ ልማቶችን የመጠገን ስራም በአፋጣኝ የሚጀመር ይሆናል።
ሰሞኑን በአስተዳደራችን የዘነበው ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ በገጠርና በከተማ ቀበሌዎች የሰዎች ህይወት አልፏል፤ የአካል ጉዳትም ደርሷል። በዚህም የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅኩ ለሟች ቤተሰቦች መፅናናት እመኛለሁ።


