ኢትዮ ቴሌኮም በድሬዳዋ አስተዳደር ለችግር የተጋለጡ ህፃናት ማቆያና ማገገሚያ ማዕከል የ 100 ሺህ ብር ድጋፍ አበረከተ

    ኢቲዮ ቴሌኮም የምስራቅ ሪጅን ‘አብሮነት በመልካም ተግባር’ በሚል በድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በተለያዩ ምክንያት ወላጆቻቸውን ያጡ፣ ተጥለው የተገኙና ለችግር የተጋለጡ ህፃናት ማቆያና ማገገሚያ ማዕከል ውስጥ ለሚገኙ ህፃናት ለ መጪው 2015 አድስ አማት የበዓል መዋያ አንድ መቶ ሺህ ብር (100,000) ድጋፍ አድርገዋል።
    ከድርጅቱ አባላት ጋር በማዕከሉ በመገኘት ድጋፉን ያስረከቡት የኢቲዮ ቴሌኮም የምስራቅ ሬጅን ዳይሬክቶሬት አቶ ጣሰው ሽመሊስ እንዳሉት ኢትዮ ቴሌኮም ከየሚያገኘው ገቢ መልሶ በተለያየ ግዜ ለህብረተሰቡ ድጋፍ የሚያደርግ ድርጅት መሆኑን ገልጸው በ2015 ዓ.ም አብሮነትን ለማጠናከር ድጋፍ የሚፈልጉ አካላትን ለይተን ለመደገፍ በያዝነው እቅድ መሰረት ዛሬ ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ህፃናት በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፉ የተደረገ ድጋፍ ነው ስሉ ቢሮው ህፃናቱ ላይ እየሰራ ያለው መልካም ስራ ስለሆነ በቀጣይም ከህፃናቱ ጎን መሆናቸውንም ገለጸዋል።
    የተደረገውን ድጋፍ የተረከቡት በድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የህፃናት ልማትና ደህንነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሪት ነዒማ ኢብራሂም የህፃናት ጉዳይ በመንግስት በጀት ብቻ ዘላቂ መፍትሄ የሚያገኝ ሳይሆን የሁሉንም ርብርብ የሚፈልግ በመሆኑ ኢትዮ ቴሌኮም ጉደዩን በመረዳት ወገን ለወገን ደራሽ ነው ብላችሁ ድጋፍ ስላደረጋችሁ በህፃናትና በቢሮው ስም እናመሰግናችኋለን ብለዋል።
    እንዲሁም እንግዶችን በመቀበል የማዕከሉን እና የህፃናት አጠቃላይ ሁኔታን ያስጎበኘ የማዕከሉ አስተባባሪ ወጣት ኢብሳ አህመድ በበኩሉ ህፃናት ወልዶ መጣል ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ መምጣቱን በመጥቀስ ድርጊቱን ለመቀነስ ህብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲኖረው ኢትዮ ቴሌኮም በአጭር የጽሁፍ መልዕክት መልዕክቶችን ተደራሽ ለማድረግ ከቢሮው ጋር ተቀናጅቶ በመስራት ለህፃናት አጋርነቱን ለማሳየት ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲሰራ መልዕክቱን አስተላልፈዋል።
    በድጋፍ የርክክቡ ላይም የቢሮው አመራሮችና ባለሞያዎች፣ የኢቲዮ ቴሌኮም ምስራቅ ሬጅን አባላት፣ የሚዲያ ባለሞያዎችና ሌሎችም ተገኝተዋል።
    የመረጃዉ ምንጭ
    የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኮሙኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ክፍል ነዉ